በታሪካዊው የአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኞች ተከላ መርሃ-ግብር በቡታጅራ ከተማ ዝግጅት ተጠናቋል።
ነገ ሐምሌ 27/2018 በአንድ ጀምበር በሀገር አቀፍ ደረጃ 800 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በተያዘው መርሃ-ግብር በቡታጅራ ከተማ ዝግጅት ተጠናቋል።
አረንጓዴ ዐሻራን ማኖር ለነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ መሠረት መጣል ነው፤ የከተማዋ ሕዝብ በነገው ዕለት በነቂስ ወጥቶ በዚህ ታሪካዊ መርሐ ግብር ላይ እንዲሳተፍ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

















