..................................................... ባገኘውት አጋጣሚ በዕድሜ የገፉ ሰዎችን በሕይወት አብዝተው ቢሰሩ ደስ ይላቸው የነበረ ነገርን ስጠይቃቸው ብዙዎቹ የሚሉኝ ነገር ይመሳሰላል። ብዙ ጊዜ የሚመጡት እነዚህ ሁለት ነገሮች ናቸው። ደግነት (kindness) እና ዘርፈ ብዙ የሕይወት ተጋላጭነት (more experience or exposure to life)። ይሄ በማንነት የሚወሰን አይደለም። በሁሉም ዓይነት ማህበረሰብ ውስጥ የማየው ነው። ደግ ሆነው ክፉ የተደረገባቸው ሰዎች ሳይቀሩ ደግ የበለጠ መሆን ሲመኙ ነው ያየውት። በእርጅና ወራታችሁ የአዕምሮ ሰላም የሚሰጣቹ ለሰዎች ያሳያችሁት ቸርነት እና ደግነት ነው። ለበደል የመለሳችሁት ግፍ እንደ ጤዛ የሚበን የእርካታ ስሜት ነው ያለው። ለክፋት ሳይቀር ያሳያችሁት ቸርነት ግን እንደ መልካም ወይን ጠጅ በየቀኑ የበለጠ ርካታ እና የሕይወት ትርጉም ይሰጣችዋል። ይሄን ሕይወት ደግ ሆናችሁ ካለፋቹ ብቻ የባከነ አይሆንም።
June 11, 2026 368