° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° የውሳኔ አሰጣጥ ሊቁ ዳንኤል ኮነመን በመጽሐፉ፡ "ልጅቷ የምትወደው ስፖርት ምንድነው ሲሉት? 'ውሳኔ ላይ መዝለል' (jumping to conclusion)" ይላል። በጣም ቀላሉ ነገር ቶሎ መፍረድ ነው። በጣም ከባዱ ሥራም መፍረድ ነው። ቶሎ መፍረድ አለመቻል ክፉ ሰዎችን ዕድል እና ጊዜ የሚሰጣቸው ይመስላል። ግን ቶሎ መፍረድ ቅን እና እውነተኞችንም ዕድል ያሳጣል። ፍትሕ ሲዘገይ ብቻ አይደለም የሚበደለው። እጅግ ሲፈጥንም ፍትሕ ሊጠቅማቸው የሚገቡ አካላትን ይጎዳል።
May 23, 2026 391 1