ናዛዚትነ እምወሐዘን ወኀይለ ውርዙትነ እም ርስዓን፣
በማሕፀንኪ ተጸውረ ብሉየ መዋዕል ሕፃን፤
ኦ ማርያም ተስፋ ለቅቡጻን ፣
በጊዜ ጸሎተ ወዕጣን ወበጊዜ ቅዱስ ቍርባን፣
ለናዝዞትነ ንዒ ኀበ ዝ መካን።
ከሐዘን የምታረጋጊን ከእርጅናም የምታድሺን (ጎልማሳ የምታደርጊን)፣
ብሉየ መዋዕል ተብሎ የተነገረለት አምላክ፣ በማሕፀንሽ ሕፃን ሆኖ ተወሰነ፤-
ተስፋ ላጡ ተስፋ የምታኾኚ ማርያም ሆይ፣
በጸሎት፣ በዕጣን እና በቍርባን ጊዜ፣
እኛን ለማረጋጋት ወደዚህ ቦታ ነይ።
[መልክአ ቍርባን]







