ውጤት ተለቋል፤ ግን ጥያቄ ቁጥር 11 ላይ ወድቃችኋል? እኔ አበበ ነኝ እንበል፤ እናንተ ደግሞ ጫላ ናችሁ!… — Bemnet Library — TG.ME

ውጤት ተለቋል፤ ግን ጥያቄ ቁጥር 11 ላይ ወድቃችኋል? 

እኔ አበበ ነኝ እንበል፤ እናንተ ደግሞ ጫላ ናችሁ! ዛሬ ሁለታችንም ጨው እንድንሠራ አንድ ዓይነት ላብራቶሪ ውስጥ ገባን። በኬሚስትሪ ሕግ ጨው ለመሥራት ሶዲየም እና ክሎሪን የተባሉ ሁለት ንጥረ ነገሮች የግድ መዋሃድ አለባቸው። እኔ ብሔራዊ ፈተና 500 ስላመጣው አንድ ትልቅ ጆንያ ሶዲየም ተሰጠኝ።ሶዲየም ሲታይ በጣም ያምራል።ነገር ግን ብቻውን ለምግብነት አይውልም።እንዲያውም ውኃ ቢነካው ይፈነዳል።

እናንተ ደግሞ ውጤታችሁ ከ300 በታች ስለሆነ የተሰጣችሁ ትንሽዬ ክሎሪን ጋዝ ብቻ ነው እንበል። ክሎሪን ደግሞ ብቻውን መርዛማ ጋዝ ነው።ሶዲየምም ብቻውን ጨው አይሆንም፣ ክሎሪንም ብቻውን ጣዕም አይሰጥም።ሁለቱ ንጥረ ነገሮች ተገናኝተው ቦንድ ካልፈጠሩ በስተቀር ለምግብ የሚሆን ጣፋጭ ጨው ማግኘት አይቻልም።

የ12ኛ ክፍል ውጤታችሁ ልክ እንደ አንዱ ንጥረ ነገር ነው።ያገኛችሁት 600 ወይም ከፍተኛ ውጤት ቢሆንም  ተግባራዊ ክህሎት ወይም ሁለተኛው ንጥረ ነገር ከሌላችሁ ውጤታችሁ ወይም ሶዲየሙ ብቻውን የሚፈነዳና ጥቅም የሌለው ነገር ሆኖ ይቀራል። ዓለም ደግሞ ሶዲየም ስላላችሁ ወይም ውጤት ስላመጣችሁ አታጨበጭብላችሁም፤ ጣፋጭ  ጨው ወይም ጥቅም እንድትሰጧት ግን ትፈልጋለች።

ይሄ ማለት ከፍተኛ ውጤት ወይም 500 ነጥብ ባገኝም ክህሎት ካሌለኝ ተወዳዳሪ አይደለሁም።ወይም ያለኝን ብዙ ሶዲየም ወደ ጨው መቀየር አልችልም።ወደ ጨው ካልቀየርኩት ደግሞ ስለማልጣፍጥ ወይም ጥቅም ስለማለሰጥ  አውጥተው ይጥሉኛል።በተጨማሪም ዝቅተኛ ውጤት አምጥታችሁና ክሎሪኑን ብቻ ይዛችሁ ከተቀመጣችሁ ክሎሪን ብቻውን መርዛማ ጋዝ ስለሆነና ጣዕም ስለሌለው በብዙ ክህሎት ባለቸው ሰዎች እየተቀደማችሁ ወደ ኃላ  ትቀራላችሁ።ግን ራሳችሁን የተለያዩ ክህሎት ብታስተምሩ ተፈላጊነታችሁ እየጨመረ፤ልክ እንደ ጨው እየጣፈጣችሁ ትሄዳላችሁ።ስለዚህ ብታልፉም ብትወድቁም ጨው ለመሆን፤ጥቅም ለመስጠትና ተፈላጊነታችሁን ለመጨመር የተለያዩ ወሳኝ ክህሎቶችን ተማሩ።ሰዎች ከእናንተ የማይርቁበት የሆነ ክህሎት ካላችሁ በየትኛውም ቦታ ተፈላጊ ናችሁ።

ፍላጎት ካላችሁ ተግባራዊ ክህሎት የሚሰጧችሁን መጽሐፎችን እንለቃለን።ፍላጎታችሁን በሪያክት አሳዩን👍

📚 @Bemnet_Library
4❤285👍106❤‍🔥11💯7🤗6👏5🙏4✍2😱2
August 26, 2026 24.9K 15 48