Bemnet Library: post #7928 — TG.ME

የ12ኛ ክፍል ውጤታችሁን ካያችሁ በኋላ ልታውቋቸው የሚገቡ 5 ነገሮች!

1,አልበርት አንስታይን፦በ16 ዓመቱ ወደ ዙሪክ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የተፈተነውን አጠቃላይ የመግቢያ ፈተና ወድቆ ነበር። ነገር ግን ያ ውድቀት ዓለምን የለወጠውን የአንጻራዊነት ሕግ (Relativity) ከመፍጠር አላገደውም።

2, ጃክ ማ የቻይናውን አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ሁለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ወድቋል። ዛሬ ግን በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ባለቤት እና የዓለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው የአሊባባ መሥራች ነው።

3,ቶማስ ኤዲሰን፦በተደጋጋሚ ጊዜ የተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ላይ በመድከሙና በመውደቁ ከትምህርት ቤት ተባሮ ነበር። እሱ ግን በውጤቱ ሳይወሰን የኤሌክትሪክ መብራትን ፈጥሮ ዓለምን አስደምሟል።

4,ሊዮ ቶልስቶይ፦ይሄ የዓለማችን ድንቅ ደራሲ፤ በካዛን ዩኒቨርሲቲ የተፈተነውን የኮርስ ፈተና ሙሉ በሙሉ ወድቆ መምህራኑ ምንም ዓይነት የመማር ችሎታ የለውም ብለው አሰናብተውት ነበር።። እርሱ ግን በሚለዮን ኮፒ የሸጡ መጽሐፎችን ፅፏል።

5,ማርክ ትዌይን የ12 ዓመት ልጅ እያለ ትምህርት አቋርጦ የወጣው ይህ ደራሲ፤ በዓለም ላይ ካሉ ታላላቅ ጸሐፊዎች አንዱ በመሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ፈተና የሚፈተኑባቸውን ታዋቂ መጽሐፎች ፅፏል።

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት በትምህርት ቤት ፈተና ወድቀው ዛሬ ላይ ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሱ ሳይንቲስቶችና ባለሀብቶች ናቸው።ስለዚህ እናንተም ውጤት ቢመጣላችሁም ባይመጣላችሁም በየቀኑ ራሳችሁን ለማሻሻል ጥረት አድርጉ፤አዳዲስ ክህሎቶችን ተማሩ፤ከምንም በላይ ደግሞ በውስጣችሁ ያለው ፍላጎት ላይ ያለማቋረጥ ስሩ።እኛ በማንኛውም ጊዜ ለእናንተ አስፈላጊ የሆኑ መጽሐፎችን እዚህ ቻናል ላይ በመልቀቅ እናግዛችኋለን።

📚 @Bemnet_Library
6❤210😢21🙏12💯10👍6🔥3🤗3❤‍🔥2✍1
August 25, 2026 23.4K 24 211