የወንድሜን አእምሮ ልጠብቅ ይገባኛል
“ስለ ባልንጀራህ ሕሊና እንጂ ስለ ገዛ ሕሊናህ አልናገርም።
— 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥29
አንድ አንድ ጊዜ እና እህቶች ስለ አለባበሳችን ስናስብ የምናስበው ያምርብናል ወይስ አያምርብኝም የሚለውን ብቻ ነው::
እግዚአብሔር ግን ከዚህ ያለፈ እንድናስብ ይፈልጋል
እግዚአብሔር አምላክ ሁላችንም አንድ አካል እንደመሆናችን መጠን አንዳችን ለሌላችን ህሊና እንድትጠነቀቅ አዞናል
ከነዚህ ነገሮች መካከል አንዱ እንደ እኔ እምነት የኛ የሴቶችን አለባበስ ይጨምራል በሁሉም ቦታ እግዚአብሔርን በመፍራት አለባበሳችን የወንድማችን ህሊና የሚጠብቅ እግዚአብሔርንም የሚያከብር መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ🙏
በክርስቶስ አካል ውስጥ ብርቱዎች ብቻ ሳይሆኑ ደካሞች አሉ:: አንቺ (እኔ ) እኛ ለራሳችን ደስታ እና ምቾት በምናደርገው ነገር ክርስቶስ የሞተለት ወንድማችን በአለባበሳችን ተሰናክሎ ሲወድቅ እንዴት ያሳዝናል 😥 ክርስቶስ ምን ይሰማው ይሆን 😥😥
1ኛ ቆሮንቶስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።
³³ ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንም ማሰናከያ አትሁኑ።
ይህ ማለት አለባበሳችን እንኳን ለእግዚአብሔር ክብር መሆን አለበት ማለት ነው 🙆♀️ ፀጋ ይረዳናል ራቁት መታየት መዞር ፋሽንእና ስልጣኔ በሚመስልበት በዚህ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ቃል በመኖር በሁለተናችን እግዚአብሔርን ማክበር ይሁንልን🙏
“እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ
“ነገር ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን የሚሉ ሴቶች ሊያደርጉ እንደሚገባ በመልካም ተግባር ይዋቡ።”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥10 (አዲሱ መ.ት)
