ታኩር በሚል የቲክቶክ ስም የሚታወቀው ልጅ ምን እንዳለ ሰማችሁ? ካልሰማችሁ እኔ ልንገራችሁ …ከዚያ ግን ከንግግሩ ምን ቁም ነገር መውሰድ እንዳለብን ቀጥሎ እፅፍላችኋለሁ:: እናንተ ብቻ በትዕግስት ተከተሉኝ…
"እዚህ ያደረሰኝ ጌታዬ ነው:: ታቃለህ:: ካድኩት በቃ በይፋ:: (ጌታየን አመፅኩት) እስካሁን ርዝቄን ያልዘጋብኝን ከለቀኩት በ )በኋላ በቃ! እስካሁን እየተፀፀትኩኝ ነው:: ብታምንም ባታምንም የተቀበልኩትን ብር እስካሁን አላጠፋሁትም…የክሊፑን ብር:: ምናልባት ሰርቼ ሃብታም ከሆንኩኝ ሰደቃ ምናምን ነው ምሰጠው:: ካልቸገረኝ አላጠፋውም አሁን::"
ከታኩር ንግግሮች መውሰድ አለብን ብዬ የማስባቸው ቁም ነገሮች …
ያው ባለፈውም እንዳልኳችሁ የ አላህ ውዴታ እያላቸው ፣ በልባቸው እስልምናቸውን እየወደዱ ነገር ግን ሁል ግዜም ከነፍሲያቸው ጋር የሚታገሉ ሰዎች እንዳሉ ማወቅ አለብን:: አንድ ሙስሊም ወንጀል ላይ ሲውል ወንጀሉን ወዶት ብቻ ሳይሆን ከራሱ ጋር ጂሃድ (ትግል) እያደረገ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ:: ከዚያ ራስን እንደ ፃዲቅ ቆጥሮ በየኮሜንት ቦክሱ አፀያፊ ስድቦችን ከመሳደብ እና ወንድሞቻችን ላይ ከመፍረድ መቆጠብ ያስፈልጋል::
ይልቁንስ በክብርና በፍቅር መገሰፅን እንልመድ:: በብልጠትና በዘዴ ወደ ቀጥተኛው መንገድ እንዲመለሱ መምከርን እናዳብር::
ሌላኛው ምንም ስኬታማ ብትሆኑ ምንም ፌመስ ብትሆኑ ከ እስልምና የሚበልጥ ሀብት እንደማታገኙ ከታኩር ንግግር መገንዘብ ይቻላል:: አላህ በሀላሉ ያብቃቃህ ብላችሁ ዱዓ አድርጉለት እስኪ!
እዚህ ደርሳችሁ ደሞ
Follow ሳታረጉኝ እንዳትሄዱ
👉https://t.me/bedru511111
March 31, 2025 3.9K 1 2