ሰውየው ለዒድ በግ ገዝተው መኪና ላይ ሊጭኑት ሲል ያመልጣል ሰውየው እየሮጡ ሲከተሉት በጉ ሚስኪን ቤት… — ኡስታዝ በድሩ ሁሴን bedru husen — TG.ME

ሰውየው ለዒድ በግ ገዝተው መኪና ላይ ሊጭኑት ሲል ያመልጣል ሰውየው እየሮጡ ሲከተሉት በጉ ሚስኪን ቤት ይገባል፣ሚስኪኗ እናት ሁሌም በር ቆመው በሰፈራቸው አንድ ሰው እርዳታ ካመጣ ብለው ይጠብቃሉ በጉ ሲገባ የበጉ ባለቤት አቡ ሙሀመድና እናት ይገጣጠማሉ እናት ሰውየው በጉን ለዒድ ያመጡላቸው መስሏቸው ለአቡ ሙሀመድ ዱዓ ያደርጋሉ አሏህ ኸይር ስራህን ይቀበልህ አሚን
አቡ ሙሀመድ በነገታው ሌላ በግ ሊገዙ ይወጣሉ በከባድ መኪና የተጫኑ ብዙ በጎች አዩ አሪፍ ያሉትን በግ መረጡ ወደ መኪናቸው አስገብተው ሊከፍሉ ሲሉ
ባለበጉ "አሏህ በዚህ አመት ብዙ በጎችን ስለሰጠኝ የመጀመሪያ ለገዛኝ ሰው በነፃ ልሰጥ ነይቼ ነበር አንተ የመጀመሪያ ነህ በጉን በነፃ ውሰድ"

https://t.me/bedru511111
March 25, 2025 3.3K 10 14