እንኳን ለ85ኛው የጀግኖች አርበኞች ብሔራዊ የድል ቀን አደረሳችሁ!
የክብር ግብዣ ጥሪ
ለዩኒቨርሲቲያችን መምህራን፣ ተማሪዎች እና አስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ፤
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም 85ኛውን የድል በዓልን (የአርበኞች ቀን) በድምቀት ለማክበር ዝግጅቱን አጠናቋል።
ይህ ታሪካዊ በዓል የአባቶቻችንንና የእናቶቻችንን ተጋድሎ የምናስታውስበት፣ ለአሁኑ ትውልድም የአርበኝነትንና የሀገር ፍቅርን ትርጉም የምናስተምርበት በመሆኑ፤ በመርሃ ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ ተገኝቶ የዝግጅቱ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን።
በዕለቱም በታሪክ ምሁራን የቀረቡ የምርምር ስራዎች፣ የምሁራን የፓናል ውይይት፣ ልዩ ልዩ ጥበባዊ ክዋኔዎች እና ከፍተኛ የተቋችን የስራ ኃላፊዎች የሚገኙበት ደማቅ መርሃ ግብር ይከናወናል።
ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም
ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ
በጥበብ ግቢ (ጥበብ አዳራሽ)
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
የአርበኞቻችንን ታሪክ በጋራ እንዘክራለን!
የውስጥ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

9
8
7May 4, 2026 13.1K 20