በሽርካ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት የደረሰባቸውን እና በአሰላ ሆስፒታሎች (በአሰላ ሆስፒታል እና በጭላሎ ሼድ ሆስፒታል) እየታከሙ ያሉትን ወገኖች ጎብኝተዋል።
እንደሚታወቀው ባለፈው ጊዜ በአርሲ ሀገረ ስብከት በሽርካ እና ማርቲ ወረዳ በታጣቂዎች በሰላማዊ ወገኖች/ምዕመናን ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከ 60 በላይ ክርስቲያኖች ኦርቶዶክሳዊያን መገደላቸው ይታወሳል። በተጨማሪም የተለያዩ የሰውነት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች/ምዕመናን በጎቤሳ ሆስፒታል፣ በአሰላ ሆስፒታል፣ በጭላሎ ሼድ ሆስፒታል፣ በአሰላ ሮሆቦት ሆስፒታል እና በተለያዩ የአዳማ ሆስፒታሎች እየታከሙ ቆይተዋል። እንዲሁም በብፁዕነታቸው መመሪያ እና አቅጣጫ ሰጪነት በአርሲ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መሪነት ሁሉም የጽሕፈት ቤት ሰራተኞች በተደጋጋሚ እነዚህን ጉዳተኞች በመጎብኘት የገንዘብ እና የሚያስፈልገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ዛሬም በብፁዕነታቸው መሪነት የሊቃነ ጳጳሳት ሌሊቱን ከአድስ አበባ በመነሳት በአሰላ ደብረ መድኃኒት ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን አቀባበል ተደርጎላቸው፣ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እንደደረሱ የቅዳሴ ስነ-ሰርዓቱን በመምራት፣ ቅዳሴው እንደተጠናቀቀ ላረፉት ምዕመናን ወንድሞቻችን የፍትሐት ጸሎት ተደርጎላቸዋል። ሕዝቡንም አስተምረዋል። በተጨማሪም ባለፉት ሳምንታት በአርሲ ሀገረ ስብከት በተፈጠረው የጸጥታ ችግር እና በአካባቢው ባሉት የጸጥታ ችግር ውስጥ በሞቱት ምዕመናን ሰፊ ምዕመናን/ሕዝብ በሐዘን ውስጥ እንደሚገኙ የሚታወቅ በመሆኑ፣ ሊቃነ ጳጳሳቱም ሕዝቡን በአግባቡ መክረውና አጽናንተው ከሐዘናቸው ጸንተው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም በአንድነት ወደ እግዚአብሔር እንዲጮሁ እና እንዲጸልዩ፣ በፍቅር እና በትዕግስት በወንድማማችነት ሕይወት መጽናት እንዳለባቸው ለሕዝቡ መልእክት አስተላልፈዋል።
ይህን መርሃ ግብር ከፈጸሙ በኋላ በቀጥታ ወደ አሰላ ሆስፒታል እና ጭላሎ ሼድ ሆስፒታል በማምራት በሽርካ እና ዲገሉና ጢጆ ወረዳ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖቻችን ጎብኝተዋል። ለሕክምናም የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፤ ለእያንዳንዱ ጉዳተኛም ጸሎት አድርገው አጽናንተዋቸዋል። ጉዳተኞቹንም የማጽናናት እና የድጋፍ ስራውም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና በቅርብ ቀናት ውስጥ የሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤው እንደተጠናቀቀ ጉዳቱ ወደ ደረሰበት ወደ ሽርካ ወረዳም እንደሚሄዱ ገልጸዋል።
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሆስፒታሉ እንደደረሱ ከጥቃቱ የተረፉትን እና በህክምና ላይ የሚገኙትን ሕፃናት፣ ሴቶች እና አዛውንቶች በአካል ሲመለከቱ በጣም አዝነዋል። በዚህም "በርቱ እናንተ ጽኑዎች ናችሁ፣ አሁንም ምንም አይደለም፣ በርቱ እግዚአብሔርም ይፈውሳችኋል፤ እኛም በሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ከጎናችሁ ነን፤ ከዚህ በላይ መጽናት እና በሃይማኖታችሁ መጽናት ይጠበቅባችዋል" በማለት ለጉዳተኞቹ ብዙ ምክር በመለገስ እግዚአብሔር ፈጽሞ እንዲፈውሳቸው ተመኝተው አጽናንተዋቸዋል።
የሊቃነ ጳጳሳቱ ጸሎትና በረከት አይለየን።
የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት
@ardssu · 849 subscribers
ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ቻናል ነው
Information
Username@ardssu
Channel history
5 events over 7 daysWe have been tracking it since September 22, 2026
We show only what we have seen ourselves.
Reincarnation on October 27, 2026
The channel changed its avatar and its topic. It may have promised its former audience something different — check the topic before subscribing.
October 27, 2026
updated its avatar — 4 times over 7 days
show each one
profile photo replaced
profile photo replaced
profile photo replaced
profile photo replaced
October 20, 2026
topic changedsimilarity to old profile 72%
These numbers aren’t from todayLast measured on October 20, 2026. The source has been silent since, so this is the last thing we saw — not the channel’s current state.
⌘K
Newest first
Share channel “የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት”
The short link opens the channel straight in the Telegram app — not in a browser tab.
tg.me/go/ardssuIs this your channel? Add @tgme as admin — and see how many people click your links. Get the stats →
















