🔴ACE SONGS #በማስተዋል ዘምሩ: post #8416 — TG.ME

ርዕስ፡ ከጥላው ወደ እውነቱ — ሙሴ እና ኢየሱስ ክርስቶስ የዕለቱ ጥቅስ፡ "ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።" — ዮሐንስ 1:17 1️⃣. ከድንጋይ ጽላት ወደ ልብ ጽላት በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ሕጉን በሲና ተራራ በድንጋይ ጽላት ላይ ጽፎ በሙሴ በኩል ሰጠ፤ ሕጉ ግን የሰውን ውስጣዊ የኃጢአት ባህርይ የመለወጥ አቅም አልነበረውም። በአዲስ ኪዳን ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ጸጋና እውነት መጣ። አሁን ሕጉ የተጻፈው በድንጋይ ላይ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በልባችን ላይ ነው (2ቆሮንቶስ 3:3)። 2️⃣. ታላቁ ነፃ አውጪ እና እውነተኛው አማላጅ ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር እና ከፈርዖን ባርነት እንደመራቸው ሁሉ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ሰውን ሁሉ ከኃጢአት፣ ከዲያብሎስ እና ከዘላለም ሞት ባርነት ነፃ አውጥቷል። ሙሴ በሲና ተራራ በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ መካከል ቆሞ ይማልድ ነበር፤ ኢየሱስ ግን በገዛ ደሙ ወደ እውነተኛዋ ቅድስት ገብቶ የዘላለም አማላጃችን እና የመካከለኛው ኪዳን አፕሊኬሽን ሆነ (ዕብራውያን 9:15)። 3️⃣. የመገናኛው ድንኳን ፍጻሜ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የመገናኛ ድንኳን እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል የመኖሩ ጥላ ነበር። በአዲስ ኪዳን ግን "ቃሉም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ" (ዮሐንስ 1:14) እንደተባለ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ በእኛ መካከል አደረ። አሁን አማኞች የእግዚአብሔር መንፈስ የሚኖርበት እውነተኛው ቤተ መቅደስ ነን። የማለዳ ጸሎት፡ ቀናቹን በፀሎት ጀምሩ መልካም ቀን Join Us @aposgroup

August 29, 2026 265