የለሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚ ወንድሞችና እህቶች በሙሉ፦ 1. በቤተክርስቲያናችን የዲጂታል ሚዲያ መመሪያ መሠረት ለማንም አገልጋይም ሆነ ምዕመን ሶሻል ሚዲያ ላይ እንዲሰብክ ፈቃድ አልሰጠችም፤ 2. በአሁኑ ወቅት በሶሻል ሚዲያ ላይ በተለይም በቲክቶክ ቤት ከፍተው የሚያስተምሩ ሁሉም ቤተክርስቲያንን የማይሰሙ አመጸኞች መሆናቸውን ማወቅ ይጠበቅባችኋል፤ 3. በአሁኑ ወቅት በቲክቶክ ቤት ከፍተው የሚያስተምሩ አብዛኞቹ አጥቢያና መጋቢ የሌላቸው (በመሪ ስር መኖር የማይፈልጉ)፥ በአጥቢያቸው ምንም አገልግሎት የሌላቸው፥ በቤተክርስቲያን ውስጥ በጽድቅና በቅድስና መኖር ያቃታቸውና የግል ዕውቅና ፈላጊዎች ናቸው። 4. በአዲሱ የቤተክርስቲያናችን የዲጂታል ሚዲያ መመሪያ ላይ በ(ሐ) ላይ "ቤተክርስቲያን ስታስተምር ከቆየቻቸው ትምህርቶች በተለየ ወይም ወጣ ባለ መልክ ሰዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ለማስተማርና ለማሳመን መሞከር የተከለከለ ነው፤" ይላል። ስለሆነም ቤተክርስቲያናችን ከ50 ዓመታት በላይ ስታስተምር ከቆየችው አስተምህሮ ወጣ ባለ መልኩ አብና ወልድ በአንድ አካል በተዋህዶ መኖራቸውን የሚያፈርስና ወልድን "ሥጋ ብቻ" በሚያደርግ የስህተት ትምህርት የሚያስተምሩ ስላሉ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን። በመጨረሻም እነዚህ ቤተክርስቲያንን የማይሰሙና ቅባትን የማያከብሩ ወገኖች በቤተክርስቲያናችን የተጻፉትን መጽሐፍት በተለይም የቢሾፕ ተክለማርያምን መጽሐፎች በትምህርታቸው ማጣቀስ የማይፈልጉ መሆናቸው እናውቃለን። በሆኑም በቤተክርስቲያናችን አውቅና የተጻፉትን መጽሐፍት በሙሉ ከቃሉ ጋር በማመሳከር እንድታነቡ እንመክራችኋለን። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን!
🔴ACE SONGS #በማስተዋል ዘምሩ: post #8407 — TG.ME
August 20, 2026 657 2