አንድሮሜዳ🇪🇹: post #1200 — TG.ME

የትኛውም ካንፓስ ቢደርሳችሁ የማታጧቸው 7 ግለሰቦች ...!


MR...ቴንሽን😂

ካንፓስ ላይ ነፍ ሙድ መያዣ ነገሮች አሉ ። አንዱ ማተሸን ነው፤ በቃ ከመሬት እየተነሱ የማይሆነ ነገር እያወሩ ያስፈራራሉ በተለይ ፍሬሽ ስንሆን ሙድ መያዣ ነው የምንሆነው ። በቃ ነገ ፈተና ተብሏል ብሎ ይደውልልሃል አንዱ ከዛ አንቺ ተሽነሽ አዳር ስታነቢ አድረሽ ጠዋት ክላስ ደፈንኩት ብለህ ሱክ ሱክ ስትል ትምህርት ራሱ የለም🥺 ። ምናምን ። ታዲያ በነዚ ወሬዎች የሚተሽን ቦቅቧቀ ሰው ሁሌ አለ ። በቃ በሆነው ባልሆነው ይንበጨበጫል ከዚ ሰው ራቁ ይዟቹሁ ገደል ነው ። የሚተሽኑ ተማሪዎች ብዙ ግዜ አንባቢ ናቸው በዛውም ልክ ውጤት ግን አይሰሩም ። ከነዚ ሰዎች ራቅ ነው ።


MR...ስፖርተኛ😭

ዶርም እስከ 8  ሰዎች ይኖራሉ በእርግጠኝነት  አንዱ ብረት ተሸካሚ ነው ። በቃ ፍጋት ያስጠላሃል 🥹። በየቀኑ ስለ 6 pack ነው ወሬው ። በሶ ካላቹሁ በቃ አለቀላችሁ በፍቅርም ሆነ በጉልበት ይጠጠባቹሃል ። ታዲያ ብዙዎች አንድ ሰሞን ይነሽጣቸዋል ደሞ ቺኮችን ለማማል ብለው😁 ። ስፓርት ከጀለስ ጋር ይጀምራሉ ግን አይቆይም ይተውታል ። ታዲያ ይቺ ጀለስ ጥቅም አላት ለስፓርቱዋ ጠዋት ስለምትነሳ ትቀሰቅሳለች ደሞ በጡንቻዋ ማስፈራራት ትችያለሽ የሚያስቸግር ካለ ።



MR አይናፋሩ😅

📚 ካንፓስ የሄዱ  ብዙዎች  ይዘውት የሚመጡት ነገር ፎንቃ ነው ። ካዲያ ሴት ተጠግቶ የማያውቀው ጀለስ ድንገት ፎንቃ ሲገባለት በቃ ተውኝ😮‍💨 ።የሌለ የሚያስቅ ነው ። ሲጃጃል ታያላችሁ ። እሷን ሲያይ አለቀ ...ቀነኒሳ መቼ ይሮጣል ። ንገራት ብላችሁ ጨቅጭቃችሁ አሳምናቹሁት ሄዶ ስለ አሳይመንት አውሮቶ ይመጣል😆 ሊያው ከደፈረ ወይ መንገድ ቀይሶ ወደ ዶረም ይሸበለላል ። ከዚ ይሰውራቹሁ ። ግን ላይፉ በተለይ የዶርም ልጅ ከሆነ ሳትስቁ አታድሩም ።

ዘረኛው ብራዘር😁

በቃ አክቲቪስት አክቲቪስት የሚያጫውተው ነው አጅሬ ። ተጨቁነን ይልሃል እየመጣ ፤  ነፃነት ይልሃል እየመጣ ....በቃ እንት ላይ እንት ሆኑ ነው ። ገደሉን ነው .... የረብሽ ግዜ ከዚ ሰውዬ መራቅ ነው ። ልታስረዳው ስሞክር አልገባህም ይልሃል.... በቃ ሳትፈልግ  ይሄ ፖተሊካ ትጋታለህ ።  ደሞ ከወደደሽ ወይ ዘሩ ከሆንሽ ሊከትብሽ የማይፈነቅለው ነገር የለም ። ተጠንቀቁ ዘረኝነት ከለከፋችሁ ...ብትሞቱ ነው ሚቀለው ። ደሞ በቀዉጢ ሰዓት ስለሆነ  ግቢ የምንገባው አዛ ነው ። ፓለቲካ አቋማችሁ ለራሳችሁ ራሱ እንዳትናገሩ ...ያለበለዚያ ውጣ በተባለ ቁጥር ወጥተህ ይሄን የፌደራል ዱላ ቀምሰህ ትመጣለህ ። ሰልፍ የካፌ ራሱ ረዘም ካለ ይቅርብህ.....ብሮ


😂the ፈላስፋው ማን

ካንፓስ ዶርም ይሄን ሰው ካገኛችሁት ዕድለኛ ናችሁ ። በቃ አለ ኣ ለሊት 7 ሰዓት ግድግዳ ላይ እያፈጠጡ ታገኙታላችሁ  ፤ ደንግጣችሁ ምን ሆነህ ?  ነው ስትሉት ክር እፈለኩ ይላቹሃል ..የምን ክር ስትሉት ?  በማወቅ እና በመማር መሀከል ያለችውን ቀጭር ክር እየፈለኩ ነው ይላቹሃል ።ወይ ደግሞ ድንገት ጠዋት 12 ሰዓት ተነስቶ ይቀሰሰቅሳችሁ እና ከመሞት መኖር እንደሚቀል ማረጋገጥ እፈልጋለሁ  ይላቹሃል ?  ይሄ ሰውዬ.. ያምሃል... ሆ ልተኛበት ባክህ ስትሉት ....ዘላለማዊ እንቅልፍ አላማረህም ይልሃል ....ይሄ ልጅ ሊወጋኝ ነው ዴ ብላችሁ እንቅልፋችሁ ጠፍቶ ስትነሱ ...ትንሽ ቆይቶ አገኘውት ብሎ ሊተኛ ይችላል ። በቃ ሲወዛገብ እያያችሁ መሳቅ ነው ። ሳትስቁ አታድሩም አልኳቹሁ ። ታዲያ እንዳትከተቡ ማዘር ዲግሪ ስጠብቅ ጨልላችሁ እንዳትጫሩ ...ዋ".!


አቶ unique😉

አጅሬን ካገኛችሁት እንዳትፋቱት በቃ አለ ኣ የምትቀኑበት አይነት ሰው ነው ።ስለ ህይወት ያለው ዕይታ ....ስለ ገንዘብ ስለ ነገሮች በቃ በተየለ መንገድ የሚኖር ስለ ሌሎቹ የማይመለከተው የራሱ LIFE ስታይል ያለው ምናምን ፐፐ አቦ በቃ ትደመማላችሁ ። እነዚ ሰዎች ትምሮ ብዙ ግዜ ይሰራሉ ግን 24 ሰዓት ሲቸክል አታየውም በቃ የሚያረገውን ያውቃል ። ጥንቁቁቅ ምናምን ዝንጥ ያለ አራዳ .....ይሄ ሰው ጓደኛ ካረጋችሁ የምር ላይፋችሁ ይቀየራል ዶርማችሁ ባይኖር ክላስ ውስጥ በእርግጥም ቢያንስ 1 አለ ጓደኛ አርጉት ስለ ህይወት ብዙ ትማራላችሁ።  many hesit አይተሃዋል በቃ ፕሮፌሰሩ ማለት ነው ። ወይም prsion break ካየየሃው ማይክል ስኮፌልድ ማለት ነው። በቃ ወጣ ያለ ነው ግን የራሱ way ያለው ነው ።

ቸካይ🙄

ይቺ ሰው የትም አለች ሰጋጭ ነች ። በቃ ህይወቱ ተመሳሳይ አዙሪት ጠዋት ክላስ ከዛ ካፌ ፤ ከዛ ላይብረሪ ፤ ማታ ዶርም አዳር ንባብ  ፤ ጠዋት ክላስ... በቃ ቅዳሜ የለ ፤ ፊልም ልይ የለ ፤ over የለ ....ወይኔ ለገነት ቁልፍ ነው ሚመስላቹ ። ቺክ ላጫውት የለ ፦ ፈተና አልቋል የለ ፤ ፍሬንዶች ይደብራቸዋል  የለ ፤ ፓሪ የለ ፤ ፎንቃሼ የለ ...በቃ ሙሉ ህይወቱ x መፈለግ ነው ። ሽምደዳ ንባብ ነው ። ለውጤት ከዚ ጋር መሆን አሪፍ ግን አድክም ንባብ አነባለው ብለሽ ማን እስከ ደም ጠብታ መታገል ይከብዳል ። ሳትንዘላዘይ ግን ፈታ እያልሽ ነው ብሮ እንጂ በገገሙ የሚሆን ነገር የለም ። ደሞ ዶርማቹ እንዲ አይነት ሰው ካለ በቃ ይጨንቃቹሃል ።ፈታ እንዳትሉ እሱ እያሰባችሁ ትተሽናላችሁ ። ያን ያክል ለውጥ ለውም መገገሙ የመጀመርያ ውጤት ስታዮ ትረጋጋላቹሁ ። ግን ይቺ ሰውዬ ስለ ፈተና ምናምን እውቀት ስለሚኖራት መጠጋቱ አሪፍ ነው ። ውጤት ታስተካክላለች ።
😁7👍4
September 24, 2024 2.5K 7