የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም ይሰጣል። - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ከዚህ ቀደም ተገልጾ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ ውይይት ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም እንዲሆን መወሰኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አረጋግጧል፡፡
በዚህም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 03/2018 ዓ.ም እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 06 እስከ 16/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ 563,858 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ 306,708 ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ እና 257,150 ተማሪዎች በማኅበራዊ ሳይንስ ለፈተናው እየተዘጋጁ መሆኑን ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ከ600 በላይ በሚሆኑ የፈተና ማዕከላት ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት የተደረገ ሲሆን፤ ፈተናው በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በሐረር ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ይሰጣል፤ በሌሎች አካባቢዎች ከኦንላይን በተጨማሪ በወረቀት የሚሰጥ መሆኑን ተጠቁሟል፡፡
Everyone be ready for Alpha Moch Championship🎉

2
1June 20, 2026 1.3K