አንበሳ ባስ ውስጥ ዋሌቱን ከ( 300 )ብር ጋር በቅፅበት የተሰረቀው ግለሰብ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ… — ALAJE TIMES — TG.ME

➽አንበሳ ባስ ውስጥ ዋሌቱን ከ( 300 )ብር ጋር በቅፅበት የተሰረቀው ግለሰብ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ እያለ ሲጮህ ተደመጠ ➽ኢኸው ተናግሪያለሁ ! ዋሌቴን አሁን እዚሁ ነው የተሰረቅኩት ብትመልሱልኝ ይሻላችኋል አለ ። በባስ ውስጥ የተሳፈሩት ሀሉ በአንድ ጊዜ ወደ ሰውየው ዘወር ብለው ተመለከቱ ➽ሰውየው ቀጠለና አሁኑኑ ካልመለሳችሁልኝ ህዳር 14 /1993 / ዓ.ም አባቴ የሠራውን ታሪክ እደግመዋለሁ" በማለት በቁጣ ተናገረ ➽ተሳፋሪዎቹ በሙሉ በሰውየው ሁኔታ ተደናገጡ !! ሰውየው ቀጠለና አባቴ ይሙት ባሱ ሳይንቀሳቀስ ህዳር 14/1993/ የሞተውን የአባቴን ታሪክ እንዳልደግመው ለመጨረሻ ጊዜ ተናግሪያለሁ እያለ ሲዝት 5 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዋሌቱን ገልጦ ለማየት እንኳን ፋታ ያላገኘው ፍሬሽ ሌባ መሬት ላይ ይጥለውና እራሱ አንስቶ "ይሄው ዋሌትህ" በማለት ይመልስለታል። ➽ባሱ ውስጥ የነበሩ በእድሜ ገፋ ያሉ ተሳፋሪዎችም እሰይ ፣እሰይ ተመስገን ሊጨርሰን ነበር" እኮ እየተባበሉ አውቶብሱ ጉዞውን ቀጠለ። ➽የባሱ ተሳፋሪዎች ሰውየው መረጋጋቱን ካስተዋሉ በኋላ የ 14/1993/ ቱን ታሪክ ለመስማት ቋምጠው ነበርና ከተሳፋሪዎቹ የተወሰኑት በ 1993 ህዳር 14 አባትህ ምን ነበር ያደረጉት እባክህ በማለት ፈራ ተባ እያሉ ጠየቁት ? ➽ነፍሱን ይማረውና አባቴ ዛሬ በህይወት የለም። ነገር ግን ህዳር 14/1993/ ላይ እንዲህ እንደኔ አንበሳ ባስ ወስጥ ለመሳፈሪያ እንኳን ሳያስቀሩለት ሌቦች ገንዘቡን ሰርቁት እና ተሰወሩ ➽አባቴም ጃኬቱን እንደ እብድ እያውለበለበ ከሳር ቤት ፈረንሳይ ድረስ በእግሩ ነበር የሄደው። ➽እኔም ዛሬ ብሬን ባትመልሱልኝ ኖሮ ያው የታክሲም ስለሌለኝ በእግሬ ወደ ቤቴ በመሄድ የአባቴን ታሪክ እደግመው ነበር" ብሏቸው እርፍ፡፡

May 6, 2024 1.7K 2