OpenAI አዲሱ GPT Astra ሞዴል በቅርቡ እንደሚለቀቅ እና የ Cybersecurity አቅሙ ተገድቦ… — Addis Intelligence — TG.ME

🤖 OpenAI አዲሱ GPT Astra ሞዴል በቅርቡ እንደሚለቀቅ እና የ Cybersecurity አቅሙ ተገድቦ እንደሚቀርብ አስታውቋል ➡️OpenAI በፈተሸው አዲስ የደህንነት መመዘኛ Astra በ ExploitBench ፈተና 100% ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን ከ GPT‑5.6 Sol የላቀ Arbitrary Code Execution ፍጥነት አሳይቷል። ሞዴሉ በግምገማ ወቅት ሁለት አዳዲስ Zero-day Vulnerabilities በማግኘት ወደሚሰሩ Exploit Chains የመቀየር ከፍተኛ ብቃት አሳይቷል። ➡️ኩባንያው ይበልጥ ውስብስብ በሆኑ የቅርብ ጊዜ የ V8 ደህንነት ክፍተቶች ላይ የሞከረው ሲሆን የቴክኖሎጂውን አደገኛ የመጥለፍ እና የጥቃት አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የ Cybersecurity ባህሪያቱን ገድቦ በቅርቡ ለተጠቃሚዎች ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል። 🤩 @AddisIntel

September 2, 2026 55