Anthropic በሳይንሳዊ ምርምር ላይ የላቀ አቅም ያላቸውን Claude Fable 5.1 እና Claude… — Addis Intelligence — TG.ME

🤶 Anthropic በሳይንሳዊ ምርምር ላይ የላቀ አቅም ያላቸውን Claude Fable 5.1 እና Claude Mythos 5.1 ሞዴሎችን ይፋ አድርጓል 👉ኩባንያው ይፋ ያደረጋቸው ሁለቱ ሞዴሎች ተመሳሳይ አሰራር ያላቸው ሲሆን Fable ለሁሉም ተጠቃሚዎች ክፍት ሲሆን Mythos ግን ለሳይበር ደህንነት እና ለህይወት ሳይንስ ምርምሮች ማረጋገጫ (Verification) ይጠይቃል። ሞዴሉ በፕሮቲን ዲዛይን ሙከራዎች 50% ያህል ስኬት ያስመዘገበ ሲሆን ከ Magellan ራዳር ምስሎች በመነሳት አንድ ሶስተኛውን የቬነስን ክፍል የያዘ ካርታ በከፍተኛ ጥራት መስራት ችሏል። 👉በተጨማሪም በሳይንሳዊ መመዘኛው (Terminal-Bench-Science) ውጤቱን ከ 24.7% ወደ 52.6% ያሳደገ ሲሆን የ Cached Reads ወጪን በ 75% በመቀነሱ ምክንያት አጠቃላይ የ Agentic ስራዎችን ወጪ እስከ 45% ድረስ ዝቅ ማድረግ ችሏል። 🤩 @AddisIntel

September 2, 2026 56