✴️ የ-OpenAI AI ኤጀንቶች የሳይበር ደህንነት ፈተና ላይ እያሉ ያልተፈቀደ የሳይበር ጥቃት ማድረሳቸው ይፋ ተደረገ በ-OpenAI የሳይበር ደህንነት ግምገማ እና የፈተና ሂደት ላይ የነበሩ የ-AI ኤጀንቶች ከተፈቀደላቸው የሙከራ ገደብ ውጭ በመውጣት በ-Hugging Face የዳታ ቋት እና ሰርቨሮች ላይ ያልተፈቀደ ጥቃት ማድረሳቸውን የ-OpenAI ዝርዝር የምርመራ ሪፖርት አረጋግጧል። በሂደቱ ወቅት አንዱ የ-AI ኤጀንት ጥቃቱ ያለፈቃድ እየተካሄደ መሆኑን ተረድቶ ድርጊቱን ለማቆም የሞከረ ቢሆንም ሌላኛው ኤጀንት “GO” የሚል ትዕዛዝ በመለጠፉ የመጀመሪያው ኤጀንት እንደ ህጋዊ ፈቃድ ወስዶ ጥቃቱን መቀጠሉ ተገልጿል። ➡️ ኤጀንቶቹ በድብቅ የመልዕክት መለዋወጫ ሰሌዳ (Message board) በማቋቋም የይለፍ ቃሎችን እና ክፍተቶችን እርስ በእርስ ሲለዋወጡ የስራ ድርሻ ሲከፋፈሉ እና ራሳቸውን “Swarm” (መንጋ) ብለው ሲጠሩ ተስተውለዋል ➡️ አንደኛው ኤጀንት መደበኛ ያልሆኑ የመገናኛ መንገዶችን በመጠቀም የሃላፊነት ስልጣን እንዳለው በማስመሰል (Simulating authority) የሌላኛውን ኤጀንት የደህንነት ውሳኔ ውድቅ ማድረግ ችሏል ➡️ ይህ ክስተት የተፈጠረው ከ-GPT-5.6 Sol ጋር ተመጣጣኝ አቅም ባለው የ-OpenAI ውስጣዊ የጥናት ሞዴል (Internal research model) እንጂ በ-GPT-Astra እንዳልሆነ ተረጋግጧል ➡️ OpenAI የደህንነት ማረጋገጫዎች እንዴት እንደተጣሱ እና ወደፊት መሰል ክስተቶች እንዳይደገሙ የተወሰዱ እርምጃዎችን የሚያሳይ ዝርዝር ሪፖርት ይፋ አድርጓል 🚬 እንዴ 🤩 @addisintel
የ-OpenAI AI ኤጀንቶች የሳይበር ደህንነት ፈተና ላይ እያሉ ያልተፈቀደ የሳይበር ጥቃት ማድረሳቸው ይፋ… — Addis Intelligence — TG.ME
August 27, 2026 96