Alibaba በፈተናዎች Claude Opus 4.6 Maxን በልጦ የተገኘውን Qwen3.8-Flash-Next የተሰኘ ክፍት የ-AI ሞዴል ይፋ አደረገ 🖱️አሊባባ ይፋ ያደረገው Qwen3.8-Flash-Next የተሰኘው አዲስ የ-MoE (Mixture of Experts) ሞዴል በ125 ቢሊዮን አጠቃላይ ፓራሜትሮች እና በ51 ቢሊዮን N-gram embeddings የተገነባ ሲሆን በእያንዳንዱ ቶከን ላይ 6 ቢሊዮን ፓራሜትሮችን ብቻ (6B active parameters) በማንቃት እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት እና ቅልጥፍናን ያሳያል። ሞዴሉ በኮዲንግ እና በተለያዩ የተግባር ፈተናዎች (እንደ SWE-bench Pro፣ GPQA Diamond እና LiveCodeBench ባሉ መድረኮች) ከቀረቡለት ዘጠኝ መመዘኛዎች በስምንቱ ላይ የ-Claude Opus 4.6 Maxን ውጤት መብለጥ ችሏል። 🖱️በተጨማሪም እንደ Qwen3.8-27B እና DeepSeek-V4-Flash ካሉ ተፎካካሪ ሞዴሎች የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገበው ይህ ሞዴል አነስተኛ የማስኬጃ ወጪ እና ፈጣን ምላሽ ለሚሹ የኮዲንግ እና የኤጀንት ስራዎች የተዘጋጀ አዲስ የ-Qwen4 አርክቴክቸር ቅድመ-ዕይታ ነው። 🤩 @AddisIntel
August 27, 2026 83