⚡️ የድርጅት ኃላፊዎች የ-AI ኤጀንቶች የሰራተኞችን የ-Slack መልዕክቶች እንዲያነቡ ይበልጥ እያበረታቱ መሆናቸው ተገለፀ የተለያዩ አለም አቀፍ ኩባንያዎች አመራሮች ሰራተኞቻቸው ከግል መልዕክት ይልቅ በይፋዊ የ-Slack ቻናሎች እንዲግባቡ ግፊት እያደረጉ ይገኛሉ። ዓላማውም የ-AI ኤጀንቶች በቂ አውድ እና መረጃ (Context) አግኝተው ንግግሮችን እንዲተነትኑ ስብሰባዎችን እንዲያጠቃልሉ የዝግጅት ገጾችን እንዲያዘጋጁ እና በውሳኔ አሰጣጥ ላይ እንዲያግዙ ለማስቻል ነው። 👉በ-Zapier ዋና ስራ አስፈፃሚ ዌድ ፎስተር (Wade Foster) ሰራተኞች በይፋዊ ቻናሎች እንዲጽፉ የሚያበረታቱ ሲሆን ከአንድ ደንበኛ ጋር በተደረገ ጥሪ ወቅት የ-AI ኤጀንትን በመጠቀም የሁለት ወራት የ-Slack ውይይቶችን ወደ ሙሉ Presentation ቀይረውታል 👉ElevenLabs በበኩሉ የውስጥ ግንኙነቱን በ-Slack ላይ በማድረግ የ-AI ኤጀንት ከ100 በላይ ይፋዊ ቻናሎች የሚወጡ መረጃዎችን አጠቃሎ ሰራተኞች ሊያዳምጡት ወደሚችሉ የ-Podcast ፕሮግራሞች ይቀይራል 👉የ-AI ኤጀንቶች ይበልጥ ጠቃሚ የሚሆኑት ሰፊ የውስጥ መረጃ ማግኘት ሲችሉ ቢሆንም የግል ውይይቶች ነፃ ሀሳብ የሚንሸራሸርባቸው በመሆናቸው አሰራሩ የስራ ቦታ ግላዊነትን (Workplace privacy) በተመለከተ ከፍተኛ ስጋት እየፈጠረ ይገኛል 🤩 @AddisIntel
የድርጅት ኃላፊዎች የ-AI ኤጀንቶች የሰራተኞችን የ-Slack መልዕክቶች እንዲያነቡ ይበልጥ እያበረታቱ… — Addis Intelligence — TG.ME
August 26, 2026 78