Meta “Hatch” የተሰኘ አዲስ የ-AI ኤጀንት እና Watermelon ሞዴልን ይፋ ለማድረግ እየተዘጋጀ… — Addis Intelligence — TG.ME

Ⓜ️ Meta “Hatch” የተሰኘ አዲስ የ-AI ኤጀንት እና Watermelon ሞዴልን ይፋ ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለፀ

የ-The Information ዘገባ እንደሚያሳየው ሜታ በመጪዎቹ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚውል “Hatch” የተሰኘ የ-AI ኤጀንት ይፋ ለማድረግ እየተዘጋጀ ሲሆን በመቀጠልም በመጪው ጥቅምት ወር “Watermelon” የተሰኘ አዲስ የ-AI ሞዴል ይለቃል ይህ እርምጃ ኩባንያው ከማስታወቂያ ገቢ ባለፈ በ-AI ቴክኖሎጂ ላይ ያወጣውን ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ወደ ቀጥተኛ የደንበኝነት ክፍያ (Subscription revenue) ለመቀየር የያዘው እቅድ አካል ነው

➡️ Hatch በ-OpenClaw ፅንሰ-ሀሳብ ላይ ተመስርቶ የተሰራ ሲሆን በወር እስከ $199.99 የሚደርስ ፕሪሚየም የደንበኝነት ክፍያ ደረጃ ሊኖረው እንደሚችል ተገልጿል

➡️ ኤጀንቱ እንደ DoorDash፣ Etsy፣ Reddit፣ Yelp እና Microsoft Outlook ካሉ የውጭ መተግበሪያዎች ጋር በቀጥታ ተገናኝቶ ተግባራትን በራሱ እንዲያከናውን ተደርጎ የተዘጋጀ ነው

➡️ ተጠቃሚዎች የጉዞ እቅድ ማውጣት የአካል ብቃት ክትትል እና ሌሎች የኤጀንት ክህሎቶችን የሚያስተዳድሩበት የተሟላ የቁጥጥር ሰሌዳ (Customizable dashboard) ይኖረዋል

ይህ እንቅስቃሴ ሜታ AIን ከተራ የውይይት ቻትቦት (Chatbot) ወደ ተጠቃሚዎች የዕለት ተዕለት ተግባራትን በተግባር ወደሚያከናውኑ ኃያላን አውቶሜትድ ኤጀንቶች ለማሸጋገር የሄደበት ትልቅ እርምጃ ነው።

🤩 @AddisIntel
👍2
August 26, 2026 116