በአዲስ አበባ የተገነቡት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች የተገልጋዩን እንግልት የሚቀንሱ ናቸው - ኢ/ር… — Addis Ababa Design And Construction Works Bureau — TG.ME

በአዲስ አበባ የተገነቡት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች የተገልጋዩን እንግልት የሚቀንሱ ናቸው - ኢ/ር አያልነሽ ሃ/ማርያም

በአዲስ አበባ የተገነቡት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች የተገልጋዩን እንግልት የሚቀንሱ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሃ/ማርያም ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ሥርዓትን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ አሠራር የሚያሸጋግሩ መሠረተ ልማቶችን የማስፋፋት ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ኢንጂነር አያልነሽ ሃብተ ማርያም እንደገለጹት፤ አዲስ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉት የተሽከርካሪ ማቆሚያ እና ተርሚናሎች የህብረተሰቡን እንግልት በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ናቸው።

እያንዳንዳቸው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጁ፣ ሙሉ በሙሉ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ልዩ ምቾትን የሚያጎናጽፉ ናቸውም ብለዋል፡፡

እነኚሁ ፕሮጀክቶችም በውስጣቸው የታክሲ እና አውቶብስ ተርሚናሎች፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጀሮች እንዲሁም የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎችን እንዳካተቱ የጠቀሱ ሲሆን በተጨማሪም የንግድ ሱቆች፣ ካፊቴሪያ እና ሬስቶራንቶች፣ የልጆች መጫወቻ እና ማረፊያ ስፍራዎች እንዲሁም ምቹ የተሳፋሪ መጠበቂያ ስፍራዎች እንደተሟሉላቸው ጠቁመዋል።

እንደ ኃላፊዋ ገለፃ ተርሚናሎቹ አሳንሰሮችን እና ንጹህ መጸዳጃ ቤቶችን እንዲሁም የደህንነት እና አደጋ ቅድመ መከላከያ ስርዓቶችም የተሟሉላቸው ናቸው፡፡

ኃላፊዋ አያይዘውም ፕሮጀክቶቹ በሙሉ አቅማቸው ወደ አገልግሎት ሲገቡ በከተማዋ ጤናማ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የተሽከርካሪ ፍሰት እና የእግረኛ እንቅስቃሴ እንዲኖር ከማስቻላቸውም ባሻገር ለከተማዋ የ«ስማርት ሲቲ» ውጥን እውን መሆን ጉልህ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል።
❤15👍10👏2
August 27, 2026 2.9K 2