የተወደዳችሁ ቅዱሳን እንኳን አደረሳችሁ።
" እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና፥ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን ትልቅ በጎነት አሳስባለሁ....በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።
ኢሳ63: 7-9
....በቀደመው ዘመን አንስቶ የተሸከመን የተባረከ ነው። ሃሌሉያ!! መሸከም...እግራችን እንዳይሰናከል... እንቅፋቱን አላመነውም! መሄድ ሲያቅተን ...የርሱ ዱካ ብቻ እየታየ .. የእኛ ዱካ የለበትም... በርሱ ትከሻ ላይ ነንና!! ዘመን ሲሻገር ይሄን የሚያዩ አይኖች የተባረኩ ናቸው። ምስጋናውን ያበዙለታል!!
“ በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱ ዘንድ ተማምኖ ይኖራል፤ ቀኑን ሁሉ ይጋርደዋል፥ በትከሻውም መካከል ያድራል።”
ዘዳ 33፥12
በርሱ ትከሻ መዋል ማደር ስለሆነልን በዘመናችን ሁሉ ጠላት ፈልጎ አጥቶናአል !!! ሃሌሉያ!!
ውዶች ሆይ:-
“እንደ ዕድሜህ እንዲሁ ኃይልህ ይሆናል።”
ዘዳ 33፥25
በተጨመረልን ዘመንና እድሜ፦ መጨመር ይሆንልን ዘንድ እዳ አለብን!!
"....ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥
በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥
እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።
እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤.."
2ጴጥ1፥5-8
በተሰጠን ዘመን የመጨመር፣ የማደግ፣ የመለወጥ ፣ የመብዛትና ሃሳቡን የማገልገል ዘመን ይሆንልን ዘንድ ከዛሬ ነሃሴ 18 - ጳጉሜ 1 2018, በሚኖረን "ጸጋውን ለመቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን እንቅረብ" በሚል መሪ ቃል ከጾም ጸሎቱ ከምልጃው እንዳንጎድል ለመገኘት እንትጋ።
" አቤቱ፥ ጠላቶችህን የሰደቡትን የቀባኸውን ዘመን የሰደቡትን አስብ።
መዝ89:51
እኛንም ዘመናችንንም እናስቀባ! እናስባርክ!!! ከቅባቱ የተነሳ ቀንበር ይሰበራልና!!
የመቀባት ዘመን ይሁንላችሁ።
@ACEBoleHermon





