ደሃም ሆነህ ጉ^ረኛና ኩራ ^ተኛ ሆነህ ከዚያም ሀብታም መሆን ያምርሃል? ዛፍና ቅጠሉ አይፈቅዱልህም:: አላህም ከማይወዳቸው ነገሮች አንዱ ነው:: ኩrat እና የወላጅ ሐቅ እዚሁ ምድር ላይ ያስከፍሉሃል ይባላል::
ዋናው ነጥቤ:- ሥራ ስትጀምሩ በኩrat አትጀምሩ:: ሥራ በነጭ ሸሚዝ አይጀመርም:: ረጅም ሱሪ ሁላ ይቆረጣል:: በቁምጣ ነው የሚጀመረው:: የሥራ የመጀመሪያው ደረጃ (phase) እንደ መኪናና አውሮፕላን ወይም ሮኬት ከባድ ማርሽ ይፈልጋል:: ዘና የምትለው ከፍታህ ስትወጣ ማለትም 40K ጫማህ ላይ ስትደር ነው:: ቅያሪ በሌለው በአንድ ጫማ ጫማ ምናባህ ሆነህ ነው የምትኮ^ራው?
ንግድ ውስጥ ስትገባ መማርህን መርሳት, ልብስህን መቁረጥ, ወጪህን መገድብ, እንቅልፍህን መቀነስ, ሽቶህን ውኃ ብቻ ማድረግ የግድ ይልሃል:: የመርካቶ ፊዚቢሊቲ ስተዲ ልንገራችሁ:: በአጭር ታጥቆ, ገላን አቆሽሾ መግባት ነው:: የጣቴ ጫፍ ላይ ያሉ ጀርሞች ከምግብ ጋር ገብተው ያሳምሙኛል የሚል ስጋት ካለብህ የሥራ ሰው አይደህም:: ሆርሞንህና ቴስቴስትሮንህ ሟሽሸዋል:: አትረባም:: ሲርበን የበ^ከተ ሥጋና አሳማ የሚፈቀድልን ሰውነታችን ጎጂ ባክቴሪያዎችን ጭምር በልቶ የበ^ክቱ ባክቴሪያ ጭምር የሚያደቅበት ረሃብ ላይ ስለሚሆን ነው:: የሥራ ረሃብ ከሌለብህ ሼም ይገድ^ልሃል ስልህ!!!
መርካቶ ከአሕያ, ከደንብ አስከባሪ, ከፒክአፕ, ከገበያተኛና ከወዛደር ጋር ተግባብቶ ለመጋፋት ነጭ ሸሚዝ አይነፋም:: ሌላ ሰፈር ላይ ብትገጨው ተኝቶ በግ ቀልበኝ የሚያስብል አደጋ መርካቶ "እያየህ ሂድ እንጂ, እያየህ አትነዳም" ላይልህ ሁላ ይችላል:: መርካቶ ለካልኩለስ ጭንቅላት ብቻ የሚሆን ስፍራ ነው:: ሌላም ቦታ አዲስ ሥራ ላይ እንደዚያ ነው:: መጥረጊያና መወልወያ መያዝ ሁላ አለብህ:: ኩ^ራትህን አኽ ፑ ብለኸው ነው የምትጀምረው::
Well, ጊዜህን ለሦስት ክፈለው፦
👉🏼 ለሥራ:- ሥራ ስትሠራ "ሞትም መዝናናትም የለም" ብለህ በሙሉ ትኩረት ሥራ።
👉🏼 ለጸሎት:- ሞትን አስታውስና ሳታበዛው ወደ ጸሎት ዙር።
👉🏼 ለእረፍት፦ 40,000 ጫማ ከፍታህ ላይ ስትደርስ "ሞትም ሥራም የሉም" ብለህ ተዝናና።
በግሌ ነጭ ልብስ እና ሱፍ በጣም ነው የምወደው:: በጣም ያምርብኛል:: ግን 40K ጫማ ከፍታ ላይ ሳልደርስ ማለትም at least basic ነገር ሳላሟላና ሥራዬ መስመር ሳይዝ በፍጹም አላስበውም:: እንደውም ልብሴ እንዲተኮስ ሁላ አልፈልግም:: ላጨማድደው እችላለሁ:: ሥራ ውስጥ ስትገባ Low profiled ሆነህ ነው የምትገባው:: አትቆለልም:: የመጀመሪያው ስቴፕ እርሻ ነው:: በግብርና ትርምስ ሞድ ትጀምረዋለህ::
አንድ ተግባራዊ ምልከታ ልጫርባችሁ::
ሽቶ ሁልጊዜ የምትቀቡ ከሆነ ገንዘባችሁ በሽቶ ያልቃል እንጂ አትረኩም:: ምክንያቱም አፍንጫችሁ ይደነዝዛል:: እናንተ ስለማይሸታችሁ ሽቶ የምትገዙት ለሰው ነው:: እንደውም አፍንጫችሁ ቶሎ ግ^ማት ይስባል:: ማለትም የግ^ማት መሴጅ ለይቶ ለአንጎል ይልካል:: ጊዜን መክፈል የግድ ነው::
@abukiweb





