🗞 የ አቡጁነይድ መልዕክቶች Abujunaid posts: post #604 — TG.ME

የድብድብ ስፖርቶች ስፖርት መስራትና ራስን የመከላከያ መንገዶችን መማር ለአንድ ሙስሊም ጠቃሚ ነገር ነው። ነገር ግን በወህይና ሸሪዓዊ ደንቦች የታጠረ መሆን አለበት። ዑለማዎቻችን እንደ ቦክስ፣ ሙአይ ታይ፣ ዊንግ ቸን፣ እና ፍሪ ስታይል ሬስሊንግ... የመሰሉ ውድድሮች ውስጥ መሳተፍን እንደሚከለክሉ ማወቅ ይገባናል። ኢብኑ ባዝ፣ አል-ዑሰይሚን እና አል-አልባኒ ቦክስንና መሰል ውድድሮችን በመከልከል ላይ ስምምነት አላቸው። የሶስቱንም ፈታዋ ዩትዩብ ላይ ይገኛል። በተጨማሪም የኢስላማዊ ፊቅህ አካዳሚ በውሳኔ ቁጥር 50 (3/10) የቦክስ ውድድር ክልክል መሆኑን በመግለፅ የክልከላውን ምክንያቶች በዝርዝር አስቀምጧል። ኡለማዎቸች ለዚህ ክልከላ ከጠቀሷቸው ምክንያቶች የሚከተሉት ይገኙበታል፦ 1. አላህ ያከበረውን ፊት መምታት፦ የተመታው ሰው ሙስሊም ይሁን ወይም ሌላ (ሰላማዊ) ሰው፣ ፊትን መምታት አይፈቀድም። ቡኻሪና ሚስሊም ከአቡሁረይራ በዘገቡት ሀዲስ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ إذا ضرب أحدكم أخاه، فليجتنب الوجه «አንዳችሁ ሲመታ ፊት መምታትን ይራቅ» (ይህ የሙስሊም ዘገባ ቃላት ነው)። በሌላ ሐዲስ እንደተላለፈውም፦ لا تضرب الوجه «ፊትን አትምቱ» ኢማም አሕመድ ዘግበውታል። ኢብኑ ሐጀር፣ አልባኒና ሌሎችም ሀሰን ደረጃ ሰጥተውታል። 2. ፀረ-ተውሒድ የመጎንበስ ልማድ፦ ለሌላ አካል ማጎንበስና መስገድ (Incline/Bow) በሸሪዓ አይፈቀድም። የሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ስለዚህ ተጠይቆ “ለሙስሊምም ሆነ ለካ_ፊ § ር በአክብሮት (ሰላምታ) መልክ በሰውነት የላይኛው ክፍል ወይም በራስ ብቻ መጎንበስ ቢሆንም እንኳ አይፈቀድም። ምክንያቱም በአክብሮት መልክ የሚደረግ መጎንበስ ዒባዳ ነው። ዒባዳ ከአላህ ብቻ በቀር ለማንም አይፈቀድም" የቋሚ ኮሚቴ ፈትዋዎች 1/171 3. ጭካኔና ነፍስን ለአደጋ ማጋለጥ፦ በጭካኔ መተላለቅና ተቃዋሚን በጣም ለመጉዳት ማለም፣ እንዲሁም በዚህ ድርጊት ማጨብጨብና መደሰት አይፈቀድም። ለዚህም ታላቁ ኢስላማዊ መርህ "መጎዳትም ሆነ መጉዳት የለም! የሚለው ነው። እንደዚሁ አንድ ስፖርተኛ በራሱ ላይ ጉዳት ማድረስና ነፍሱን ለጥፋት መዳረግ አይፈቀድለትም፣ ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏልና፦ ﴿وَأَنفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةِ﴾ በአላህም መንገድ ለግሱ፡፡ በእጆቻችሁም (ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና) አልበቀራ 195 እውነታውን ካጤንን በርካታ ቦክሰኞች በጨዋታ ወቅት በሚደርስባቸው ጉዳት ለሞት ተዳርገዋል፣ ለዚህም አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ ተቆርቋሪዎች እንኳ ድርጊቱ እንደ ስፖርት እንዳይታይና እንዲታገድ ሲጠይቁ ይሰማል። 4. ተጨማሪ ጥሰቶች፡– ኡለማዎች በተጨማሪ፤ የሰውነትን private ገላ (ዓውራ) መግለጥ፣ ሙዚቃ፣ ኢኽቲላጥ፣ ግዜን ማጥፋትና መሰል ተጨማሪ ጥሰቶችንም ዘርዝረዋል። ጥንቃቄ፡‐ እነዚህን ውድድሮች ወደ "ሃይማኖታዊ ፉክክር" መቀየር እንዲሁም የሃይማኖት መገለጫ ዒባዳዎችን ከውድድሩ ውጤት ጋር ማያያዝ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል። ዲን (ያውም ባልተፈቀደ ጨዋታ) ሊነሰር አይችልም። ይህን ተከትሎ ብሽሽቅ ውስጥ በግባት ሌላ ጥፋት ነው። ዲናችን ከዚህ ሁሉ በእጅጉ የጠራና የላቀ ነው! ለወጣቶቻችን ያለኝ ምክር፦ ነገሮችን በሸሪዓ ሚዛን ሳትመዝኑ አታጨብጭቡ። ህይወታችን ሁሉ ለአላህ ይሁን የሚል ነው። {قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ} «ስግደቴ፣ መስዋዕቴ፣ ህይወቴና ሞቴ ለአለማቱ ጌታ ለአላህ ብቻ ነው በሉ።» አላህ የበለጠ ያውቃል አበጁነይድ 18/8/2018

👍17
April 26, 2026 1.6K 18