🗞 የ አቡጁነይድ መልዕክቶች Abujunaid posts: post #596 — TG.ME

አሊምም ይሁን ተራ ሰው ሲሞት መቀበር ያለበት በሙስሊሞች መቃብር ብቻ ነው። ይህ ደግሞ ሶሐቦችና ሰለፎች ሁሉ የነበሩበት ተጨባጭ ነው። عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله ﷺ قال «لا تجعلوا بيوتكم مقابر....» رواه مسلم، 1/539 ሙስሊም ከአቡሁሑረይራ በተዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ (ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ... ) በማለት የተናገሩትን በማስመልከት አልሐፊዝ ኢብኑ ሐጀር «ሐዲሱ በግልፅ የሚያመላክተው፤ በማንኛውም መልኩ በቤት ውስጥ መቅበር እንደተከለከለ ነው» ብለዋል። [ፈትሁልባሪ 1/130] ይህ ግንዛቤ የአል ሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር ብቻ አልነበረም። ለሽርክ መስፋፋት ምክንያት እንዳይሆን ወይም ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች ጋር ላለመመሳሰል እና መሰል ምክንያቶች ብዙ የኢስላም አዒማዎች ይህንን ተግባር ከልክለዋል። በተለይ ደግሞ በማህበረሰብ ውስጥ ትልቅ ክብር የሚቸረው ሰው ሲሆን ክልከላው ይጎላል። ምክንያቱ ደግሞ በተውሒድ ላይ የሚደቀነው አደጋ የከፋ ስለሚሆንና ብዙ መዘዞችን ስለሚያስከትል ነው። ወደ ጥፋት የሚያዳርሱ መንገዶችን መዝጋት (ሰድዱ ዘራኢዕ) ታላቅ መርሆ መሆኑ አያጠያይቅም። አል ኢማሙ አሽሻጢቢይ እንዲህ ብለዋል፤ <መሰረታቸው ፍቁድ (ሙባህ) እንኳን ቢሆን ወደ ክልክል ነገር የሚያዳርሱ ከሆነ መከልከል ግዴታ ነው። ስለዚህም ጥንቃቄ ይፈልጋል። በተለያዩ ግዜያት የተንሰራፉ መጤ እምነቶች መነሻቸው ቀለል ያለ ከገር ነበር። ተሰሚነት ያላቸው ኡለማዎችና ዱዓቶች የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል። ወላሁ አዕለም ---------------- 📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች @abujunaidposts

October 19, 2025 4.4K 19