«ደመናው ያልፋል፤ ፀሐይዋ ትወጣለች»
በክረምት ወቅት ሰማዩ በጨለማና በከበዱ ደመናዎች ይሸፈናል። ፀሐይ ሳትወጣ ቀኑ በጭጋግና በዝናብ ሊያልፍ ይችላል። ነገር ግን ያ ደመና እስከ ወዲያኛው አይኖርም።
ዝናቡ ሲጥስ፣ ደመናው ሲገፈፍ፣ ሰማዩ ይበልጥ የጠራና ፀሐይም ይበልጥ ደምቃ ትወጣለች።
በመንፈሳዊ ህይወታችንም የሚገጥሙን ፈተናዎች፣ ድካሞችና የመከራ ወቅቶች እንደ ክረምት ደመና ናቸው።
አንዳንድ ጊዜ አምላክ የራቀን፣ ህይወታችንም በጭጋግ የተከበበ ሊመስለን ይችላል።
ነገር ግን በጽናት ካለፍነው፣ ፈተናው ሲያልፍ መንፈሳዊ ማንነታችን ይበልጥ የጠራና የበረታ ይሆናል።
"እንባ ምሽት ይቆያል፤ ደስታ ግን በማለዳ ይመጣል።" (መዝሙር 30፥5)
@abufkr1621





