የአከራይና ተከራይ ውል እድሳት ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀሩት ፤ ሳይረፍድብዎ ውልዎን ያድሱ !
ከሀምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባና እድሳት አገልግሎት እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ የሚቆይ በመሆኑ ፣ የተሰጠው ጊዜ ሊጠናቀቅ አነስተኛ ቀናት ቀርተውታል።
ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመቅረብ አከራዮችና ተከራዮች ውላቸውን እያደሱ ቢሆንም በመጨረሻዎቹ ቀናት ሊደርስ ከሚችል መጨናነቅ እንዲሁም ጊዜው ካለፈ በኋላ የሚያጋጥሙ የቅጣት ውሳኔዎችንና አላስፈላጊ የህግ መተላለፎችን ለማስቀረት ቀሪዎቹን ቀናት በአግባቡ መጠቀም አስፈላጊ ነው።
ውል ማደስ የሚያስገኛቸው ዋና ዋና ጥቅሞች፦
ህጋዊ ከለላ ያገኛሉ፦ አከራይም ሆኑ ተከራይ መብትና ግዴታቸውን በህግ ጥላ ስር ያረጋግጣሉ።
አላስፈላጊ አለመግባባቶችን ይቀርፋሉ፦ የኪራይ ተመንና የውል ዘመንን በግልጽ በመደንገግ ሰላማዊ አብሮነትን ይፈጥራሉ።
ቅጣትን ያድናሉ፦ ሁለት ዓመት የሞላቸው ውሎች ሆነው በተቀመጠው ገደብ (ነሐሴ 30) ካለደሱ ለህጋዊና አስተዳደራዊ ተጠያቂነትና ለተጨማሪ ቅጣት ስለሚያጋልጡ ውል ማደስዎ ከነዚህ ቅጣቶች ያድናል።
ትኩረት፦ የምዝገባ ጊዜው ከተጠናቀቀ በኋላ ምንም አይነት ተጨማሪ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ፣ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያዎ ወደሚገኘው የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመቅረብ ውልዎን እንዲያድሱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ሕጋዊ ውል — ለሰላማዊና ለተረጋጋ አኗኗር መሠረት ነው!
ነሀሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aahdab

August 24, 2026 8.3K 21