5 ቀናት ብቻ ቀሩት!" ውድ የመኖሪያ ቤት አከራዮች እና ተከራዮች፤ ጊዜው እየፈጠነ ነው!! የአዲስ አበባ… — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU — TG.ME

"5 ቀናት ብቻ ቀሩት!"

ውድ የመኖሪያ ቤት አከራዮች እና ተከራዮች፤
ጊዜው እየፈጠነ ነው!!

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ያስቀመጠው የአከራይ ተከራይ የውል እድሳት ጊዜ ሊጠናቀቅ 5 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

ለምን ውል ማደስ ያስፈልጋል?

የሁለቱንም ወገን ሕጋዊ መብት ለማስከበር

የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ደንብን (11.5%) አክብሮ
ለመስራት

ከተጨማሪ ቅጣት እና አላስፈላጊ እንግልት
ለመዳን

አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታ፦

በየክፍለ ከተማው ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤቶች ፤ በየወረዳው እና በሁሉም የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት መስጫዎች በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት

"አሁኑኑ ውላችሁን በማደስ ሊያጋጥሙ ከሚችሉ አላስፈላጊ ቅጣቶች እና እንግልቶች ራሳችሁን ጠብቁ!”
August 31, 2026 6.8K 32