በራስ አቅም ሰበዓዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ
#AAFDRMC_ጥር 9/2018ዓ.ም
በእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የየካ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የአደጋ ስጋት ምክር ቤት በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር በራስ አቅም ሰበዓዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ፤ በመጋዘን ፕሮጀክት እና በምግብ ክምችት ያለበትን ደረጃ ለማወቅ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ጠቅላላ አመራር በተገኙበት ጥልቅ ግምገማ አደረገ።
በመድረኩ የተገኙት የየካ ክ/ከተማ ክቡር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍጹም ኃይሌ እንዳሉት ማንኛውንም ዓይነት ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎችን በመከላከልና የመቋቋም አቅማችንን በማሳደግ፣ በራሳችን ጥረትና ድካም እየተረዳዳን ለዘላቂ ልማት መትጋት ይገባል። አዲስ አበባ በሁለተናዊ ብልፅግና የማድረግ አቅሟ ከእለት እለት እየጨመረ አይቻሉም የተባሉ ተግባራቶችን በድል እያጠናቀቀች የምትገኝ ከተማ ነች። በመሆኑምይህ የከተማችን ከተረጅነት የመላቀቅ ፕሮጀክት በራስ አቅም የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ወሳኝ እንደ መሆኑ መጠን፣ ከራስ አልፎ ሕዝብን የሚጠቅም መልካም እና የተቀደሰ ዓላማ በመሆኑ በራስ አቅም የሚደረግ ሰብዓዊ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ልመናና ተረጂነት ስንፍናን የሚያስፋፉ፣ ሰብአዊ ክብርን የሚነኩና ዘላቂ ልማትን የማያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።
በመሆኑም ሕዝባችንን ይዘን መንግስታዊና መንግስታዊ ተቋማትን በማስተባበር እጅግ በአጠረ ጊዜ በራስ አቅም ሰብዓዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ይገባል። በዚህም የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት የግድ ይላል። በተለይም የትምህርትና የሃይማኖት ተቋማት ይህንን የተረጂነትና የልመና አስተሳሰብ በመለወጥ ረገድ ዋነኛ ተዋናይ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ሲሉ የማጠቃለያ ሀሳብና መልእክት አስተላልፈዋል።
በመድረኩም የተሳተፋ አመራሮች ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት የተቀመጠውን የከተማ አቅጣጫ ለማስተግበር ቃል በመግባት የአደጋ ተጋላጭነትን በማስቀረት፣ የአደጋ ዝግጁነትን በማጠናከርና ምላሽ ሰጪነትን በማሳደግ በኩል እንደ ሀገር የተጀመረውን የአሰራር ለውጥ ለማስቀጠል እንደ ምክር ቤት አባልነት የተረጂነትን አሉታዊ አስተሳሰብ በመለወጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥም ግንባር ቀደም ሚናውን ለመወጣት የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸው ከሰጡት ሀሳብና አስተያየት መረዳት ተችሏል።
January 20, 2026 693