የዳግማዊ ምኒሊክ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን አጠናክሮ እየሰጠይገኛል።… — Addis Ababa Health Bureau / አዲስ አበባ ጤና ቢሮ / AACAHB / — TG.ME

የዳግማዊ ምኒሊክ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን አጠናክሮ እየሰጠይገኛል።

አ/አ/ጤና ቢሮ ነሐሴ 19 2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ስር የሚገኘው የዳግማዊ ምኒሊክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኬሌጅ በጌርጌሴኖን የአዕምሮ መርጃ ማዕከል በመገኘት የተለያዩ ድጋፎችን ማድረግ ችሏል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የኮሌጁ ኃላፊዎች ፣ ሰራተኞች እና የኮሌጁ ተማሪዎች በመገኘት ነፃ የህክምናና የዓይነት ድጋፍ እንዲሁም የንጽህና በጎ ተግባር አከናውነዋል።

ኮሌጁ ድጋፉን ያደረገው ከኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማህበር /EPHA/ ጋር በመተባበር ነው።

የዳግማዊ ምኒሊክ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ አለሙ ዳንኤል ኮሌጁ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

በማሀበረሰቡ ውስጥ ያሉ ችግሮችን በጥናት በመለየትና የመፍትሄ ሃሳቦችን ማመላከት የኮሌጁ ዋነኛ ተልዕኮ መሆኑን የገለፁት አቶ አለሙ ዳንኤል በጌርጌሶኖን የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል የተደረገው ድጋፍ የዚሁ አካል ነው ብለዋል።

ኮሌጁ ከመማር ማስተማርና ከምርምር ሥራዎች ጎን ለጎን የማህበረሰብ አገልግሎት በተለይም የአእምሮ ጤና ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የተናገሩት አቶ አለሙ ዳንኤል ተመሳሳይ ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመልክተዋል።
❤4
August 25, 2026 2.6K