ቃ ላ ት | 𝚀 𝚊 𝚕 𝚊 𝚝: post #55 — TG.ME

— 3 ዓመታት — ከሕይወት ላይ ከአንድ ሺህ አንድ ሌሊቶች በላይ አልፈዋል። እንደ ዘበት 14 ቅጾች ፣ 717 ገጾች በዲጂታል ታትመው እናንተ ጋር ደርሰዋል። ከእያንዳንዱ ዕትም ጀርባ ረዣዥም የእግር መንገዶች በእቅድ ፣ የካፌ ውስጥ ጨዋታዎች፣ ዘለግ ያሉ የስልክ ውይይቶችና የጽሑፍ መልእክት ልውውጦች ተደርገዋል። እንደ ወዳጅ በእኔነት ስሜት በምናዋጣቸው ሃሳቦች ላይ (for a better out come) ተጨቃጭቀናል። እዚህ ጋር ብዙ የመታከትና መሰላቸት ስሜት አስተናግደናል። እንደ ወረደ ተጽፎ የወጣ ጽሑፍ የለም። የተሰረዙ፣ የተደለዙ፣ የተከለሱ (rewrite የተደረጉ) ጽሑፎችና መሥመሮች እልፍ ናቸው። እያንዳንዱ ቅጽ እንደ ይዘቱና እንደ መልኩ በተለያየ ሒደት (process) ውስጥ ያልፋል። ያ በሆነ መንገድ አይለመድም። ትጋት የሚጠይቅ ጉዞ ነበረው። ከጊዜ፣ ከዕንቅልፍ እና ጉልበታችን ላይ ያለስስት ሰርቀናል። በግል ጉዳይና ሩጫ ተጠምደን ከቃላት ጋር ስንጠፋፋም እንነፋፈቃለን። እንዛዛታለን : ) ለሕልማችን ረብ፣ ትርጉም ለሚሰጠን ድካም አልሰነፍንም። ምክንያት — will power እና ከእናንተ የሚደርሱን የማበረታቻ መልእክቶች ናቸው። በቃላት መጽሔት ቅጾች ውስጥ ውብ መጣጥፋችሁን ያጋራችሁን፣ ለቃለ መጠይቅ ፈቃድ በመስጠት የተባበራችሁንን ጸሐፊያንን፣ እንዲሁም አስተያየታችሁን የምታደርሱንን አንባቢያን እናመሰግናለን። ደግሞም እንቀጥላለን🥂 … ቃላት 14 ዛሬ ምሽት ይጠብቁን።

❤64🔥7👏5👍3
May 2, 2025 5.3K 4