የዎላይታ ሶዶ ወላጆች በግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ጭማሪ መማረራቸውን ገለፁ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች በቅርቡ ያደረጉት የትምህርት ክፍያ ጭማሪ ለወላጆች ከባድ የኢኮኖሚ ጫና መፍጠሩን ወላጆች ለ WT Media የገለፁት ቅሬታ ያሳያል።
እንደ ወላጆች ገለጻ፤ ከ2018 ዓ.ም. ሰኔ ወር ወዲህ ባሉት ሁለት ወራት ውስጥ ብቻ ከቅድመ መደበኛ (KG) እስከ ከፍተኛ ክፍሎች ያሉ የትምህርት ክፍያዎች ያለምንም ግልጽ ምክንያት "በእጥፍ" መጨመራቸው ተነግሯል።
ይህ ድንገተኛ እና ከፍተኛ ጭማሪ በተለይም በኑሮ ውድነት ለሚማቅቁ ቤተሰቦች ከባድ ፈተና እንደሆነባቸው ወላጆች በምሬት ይገልጻሉ።
ወላጆች ይህንን አግባብነት የሌለው የክፍያ ጭማሪ በተመለከተ ጭማሪው ግልጽ በሆነ ምክንያት ያልተደገፈ መሆኑን እና በሁለት ወራት ልዩነት ብቻ በእጥፍ ማደጉ ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ ጠቁመዋል።
የከተማ አስተዳደሩ እና የሚመለከታቸው የትምህርት ዘርፍ ተቆጣጣሪ አካላት ጉዳዩን በአስቸኳይ መርምረው መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።
በተጨማሪም የትምህርት ቤቶች የክፍያ ጭማሪ ከሕግና ደንብ ጋር የተጣጣመ መሆኑን እንዲያረጋግጡ እና የወላጆችን ብሶት በመረዳት የከተማው አስተዳደር ተገቢውን ቁጥጥር እንዲያደርግም ጥሪ አስተላልፏል።
Voice of Marginalized Community - WT Media
#Ethiopia #Wolaita #WolaitaSodo #WTMedia
Read more on our official website 👇
https://wolaitatimes.com/?p=8183