UAT Tutorial Official: post #13171 — TG.ME

🔥 ስለ Government sponsorship፣ Self sponsorship እንዲሁም ስለ Presidential scholarship ተገቢ የሆነ መረጃ አላችሁ ብለን ተስፋ አለን። ከሌላችሁም @UATsupport ላይ ጠይቁን።

አምና የተዋወቀ አዲስ Program ነው 👉 Teachers Education Scholarship

📌 ይህ Scholarship የሚሰጠው በ2018 ዓ.ም የ2ተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው የማትሪክ ፈተናን በተሳካ ሁኔታ ላለፉ 500 ተማሪዎች ብቻ ነው።

ይህ Scholarship ለ 5 አመት የተቀናጀ ቅድመ ምረቃን እና ድህረ ምረቃን የሚመራ program ሲሆን ተማሪዎች የተፈጥሮ ሳይንሶችን፣ ማህበራዊ ሳይንሶችን እና ቋንቋዎችን ጨምሮ የተለያዩ ዘርፎችን ያስተምራል።

የዚህ Scholarship ጥቅሞች ምን ምን ናቸው?

📌 የትምህርት ወጪን እንዲሁም ከትምህርት ጋር የተያያዙ የተለያዩ ወጪዎችን ሙሉ ለሙሉ ይሸፍናል።

📌ለኑሮ እና ትምህርታዊ ወጪዎችን ለማገዝ መጠነኛ የሆነ የኪስ ገንዘብ ይሰጣል

📌ሙያዊ ብቃትን እና የትምህርት አመራርን ለመገንባት የተነደፈ ከፍተኛ ጥራት ያለው የመምህራን ስልጠና ማግኘት ይችላሉ።

🔥 ይህን Scholarship የሚያገኙ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ከተመረቁ በኋላ ቢያንስ ለ5አመታት በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ ለማገልገል ቃል የሚገቡበትን መደበኛ ስምምነት መፈረም ይጠበቅባቸዋል።

@UATTutorialofficial
❤5
August 24, 2026 1.8K 10