UAT Tutorial Official: post #13156 — TG.ME

Havan Academy🤗የግል የውጤት ቀን ታሪኬን ላጫውታቹህ እስኪ። የ2015 የኢንትራንስ ተፈታኝ ነበርኩ። እቅዴ ከኢትዮጵያ የመጀምሪያዉን ዉጤት ማስመዝገብ ካልሆነም ከ640 በላይ ማምጣት ነበር። ምኞት አይከለከል አይደል። ታዲያ ይሄ እንደማይሆን ያወቁት ገና የመጀመሪያውን ትምህርት ፈተና (English) እንደወሰድን ነበር። ጥሩ ልሰራው ይቅርና ሙሉ ጥያቄዉን ልጨርሰው አልቻልኩም ነበር። በመጨረሻም ዎርክሽቱን ሳላይ…
የቀጠለ...

የግል የዉጤት ቀን ታሪኬ

በመጀመሪያ ሁላችሁንም ላሳያችሁኝ ፍቅር ከልብ አመሰግናለው። እንዲህ ይሆናል ብየ አልጠበኩም ነበር።🙏 እንቀጥል።

...ዉጤት ሌሊት 6 ሰአት ይመጣል ተብሎ እየጠበቅን ነበር። እንደምንም 6 ሰዓት ላይ ብንደርስም ዉጤት አየው የሚል ተማሪ ግን አልነበረም። ያለምንም ስኬት ስልኬ ጋር ስታገል፣ ጓደኞቸ ጋር ስደዋወል ባትሪዋ ዘጋ። ያኔ ሌሊት ይሁን ቀን የሚጠይቅ ሰው አልነበረም። ሌሊት 8 ሰዓት ላይ ጓደኞቸ ጋር ተደዋዉለን አናወራለን።

እኔ የምኖርበት አካባቢ መብራት የለም። ለትንሽ ጊዜ ጨለማው ጋር ከተማከርኩ በሁዋላ በነጋታው በአቅራቢያችን ካለች ትንሽየ ከተማ ከሚኖር ጓደኛየ ጋር ሄጀ ስልኬን ልቸርጅ ወሰንኩ። ጓደኛየም የ12ኛ ክፍል ተማሪ ስለነበር ዉጤት አብረን እናያለን።

ያለመደብኝን ማታ 9፡30 የተኛው ሳይነጋ 11፡30 ሰአት ተነሳው። ከ1፡30 የእግር ጉዞ በሁዋላ ጓደኛየ ቤት ደረስኩ።ምንም የተፈጠረ ነገር አልነበረም። ዉጤቱን ያየ ተማሪም አልነበረም። ሁለት ሁነን የኔንም የርሱንም በቴሌግራም ቦት፣ በSMS እና በwebsite ስንሞክር አረፈድን።
ከጠዋቱ 3 ሰዓት ሆነ ዉጤታችን አሁንም አላየንም። 5 ሰዓት ሆነ አሁንም አልሰራልንም። በመጨረሻም እስከ 6 ሰዓት ሞክረን አልሳካ ቢለን ስልካችንን ጥለነው ወደወንዝ ወረድን።
ጓደኛየ ምኞቱ ማለፍ ብቻ ነው። "ብቻ ልለፍ ምንም እኮ ለፈተናው አልተዘጋጀዉም አንተ። ቀልጀበታለው ባክህ" ይለኛል

ወንዝ ወርደን የክረምት የአክራሞታችን ስናወራ፣ ስንቀላለድ፣ ስንከራከር ስለዉጤታችን ረስተነው ነበር። (ይህ ሁሌም የሚያጋጥም ነገር ነው። ዉጤት በተባለው ሰዓት ወዲያውኑ ላታዩ ትችላላችሁ።) ቆይታችን አልቆ 9 ሰዓት አካባቢ አዲስ ሁነን ወደቤት ተመለስን።

ስልክ ተደዉሎልኝ ነበር። እስካሁን ስንደዋወል ዉጤታችን ስላልመጣ ስለመግለጫው አንዳንድ ነገሮችን እያነሳን እናወራ ነበር።ስልኬ ጠራ። የኛ ጁኒየር የትምህርት ቤታችን ተማሪ ነበር። እነሱም ዉጤታችንን በጉጉት ነው ሚጠብቁት። "እንኳን ደስ ያለህ ጆሲ" አለኝ እየተፍለቀለቀ። "ዉጤት አያቹህ እንዴ?" ስለው ተገርሞ 641 እንዳመጣው አበሰረኝ። ከዚያማ ከጓደኛየ ጋር በRonaldo style "Suuiiii..." ብለን Celebrate አደረግን። I was so glad. 🥳

ነገር ግን ጓደኛየ ገና አላየም ነበር። በዚህ አመት ያለፈው 3 በመቶ ብቻ ነው ስለተባለ በጣም ተጨንቋል።እኔም ለሱ ተጨነቄያለው። ወዲያው የሱንም አየን። 367 ነበር።
ኡፍፍፍፍፍ...Suuuiiii...yes...Thank God... መተቃቀፍ፣ መሳቅ... ለ10 ደቂቃ ያክል ወጣልን። እንደዛች ቀን ደስ ብሎኝ የሚያውቅ አይመስለኝም።

ከዚያ በሁዋላ ለወንድሜ ነገርኩት። እሱም ለዘመድ አድማዱ ዜናውን ስለዘራው ሁሉም ይደውልልኝ ጀመር። ቀኑ ስለመሸ ከጓደኛየ ጋር ተለያይተን ወደቤቴ ተመልስኩ።
ቤተሰቦቼ በጣም ኮርተዉብኛል። "ካስተማሩ አይቀር ልጅ እንዲህ ነው እንጂ" ይባባላሉ።

የትምህርት ቤቴ ጓደኞቸ ጋር እየተደዋወልን የእያንዳንዳችንን ዉጤት መጠያየቅ ተያያዝነው።

ለእናንተም ነጋችሁን እንደኔ እና እንደጓደኛየ የምትፈኩበት ቀን ያድርግላችሁ!!

አሜን በሉ። 🤞

Join @UATTutorialofficial
❤33🙏16
August 23, 2026 2.1K 10 6