UAT Tutorial Official: post #13138 — TG.ME

Forwarded fromHAHavan Academy
🤗የግል የውጤት ቀን ታሪኬን ላጫውታቹህ እስኪ።

የ2015 የኢንትራንስ ተፈታኝ ነበርኩ።  እቅዴ ከኢትዮጵያ የመጀምሪያዉን ዉጤት ማስመዝገብ ካልሆነም ከ640 በላይ ማምጣት ነበር። ምኞት አይከለከል አይደል።
ታዲያ ይሄ እንደማይሆን ያወቁት ገና የመጀመሪያውን ትምህርት ፈተና (English) እንደወሰድን ነበር። ጥሩ ልሰራው ይቅርና ሙሉ ጥያቄዉን  ልጨርሰው አልቻልኩም ነበር። በመጨረሻም ዎርክሽቱን ሳላይ የመስሪያ ወረቀቱ ላይ ማጥቆር ጀመርኩ። በእድል ባገኝ ብየ ነው።😁

ሁሉንም ትምህርት ተፈትነን እንደጨረስን እንደኔ የተናደደ ሰው ያለ አይመስለኝም። ከጓደኞቸ ጋር መግባባት አቅጦኝ ሌላ ሰው ሁኘ ነበር። ራሴን እንደምንም አረጋጋሁትና ከጓደኞቸ ጋር የወደቅነዉን ለማየት ሞከርን።

ክረምቱን ከቤተሰብ ጋር ነበርኩ። ታዲያ ካሰላሁት ዉጤቴ ላይ አንዴ ስጨምርበት፣ አንዴ ደግሞ ስቀንስበት በመጨረሻም  የዉጤት መዉጫ ቀን ደረሰ።
እንደምንም 600 ቤት ብገባ ብየ ጠንክሬ   እየጸለይኩ ነው። ስለቱንም በላይ በላይ እሳለዋለው። 🙏
ከኛ በፊት ከ600 በላይ ያመጡ ተማሪዎች የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እና የዉጭ የትምህርት እድል ተበርክቶላቸው ነበር። እኔም አመቱን ሙሉ ያጠናሁት ለዚህ ነበር።

የመግለጫው ቀን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሴቶች፣ በወንዶች፣ በ አዲስ አበባ፣ በ ሃረሪ...፣ሙሉ ያሳለፉ፣ ምንም ያላሳለፉ እያለ ይተነትነው ገባ።
ለኔ መርዶ የሆነብኝ ግን ከፍተኛ ዉጤት 649 ነው የሚለው ነበር። "ይሄ ማለት ዉጤት ከጠበቅነው በታች ነው ሚመጣው" አልኩ። ከኛ በፊት ከፍተኛ ዉጤት 666 ስለነበር 640 ቤት ብዙ ሰው አምጥቶ ነበር። ፍርሃቴ ይባስዉኑ ጨመረ። 600 ሳልገባ እየቀረው ነው።

"ይህ ዉጤት የዓለም መጨረሻ አይደል፤ ህይዎት እንደው ይቀጥላል" እያልኩ ራሴን ለማረጋገት ብሞክርም እጢዎቼን ላብ ከማመንጨት፣ ልቤን እና ሳንባየን በፍጥነት ከመምታት ልታደጋቸው አልቻልኩም። አንዳንዴማ ብርድ ብርድም ይቃጣኛል።

ልቀጥለው እንዴ...?

Join: @HavanAcademyOfficial
❤26
August 22, 2026 2.1K 7 7