የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና (UAT)
የፈተናው ሁኔታ፦ 100 ባለብዙ ምርጫ ጥያቄዎች በኮምፒውተር ይወሰዳሉ። አጠቃላይ ሰዓት፦ 2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ።
የቃልና የማመዛዘን ክፍል፦ 55 ጥያቄዎች (60 ደቂቃ)። ንባብ መረዳት፣ ቃላት እና ሰዋሰው ይፈትናል።
የቁጥርና የሂሳብ ክፍል፦ 45 ጥያቄዎች (60 ደቂቃ)። የሂሳብ ስሌት፣ ዳታ ትንተና፣ አልጀብራ እና ችግር መፍታት ይፈትናል።
ህግ፦ የተሰጠው ሰዓት ሲያልቅ ክፍሉ በራሱ ይዘጋል። ወደ ኋላ መመለስም ሆነ ዘሎ ማለፍ አይቻልም።
የሚፈቀዱ ቁሳቁሶች፦ ህጋዊ መታወቂያ፣ የመፈተኛ ቲኬት፣ መደበኛ ካልኩሌተር፣ እስክሪብቶ እና እርሳስ።
የተከለከሉ ቁሳቁሶች፦ ስልክ፣ ስማርት ሰዓት፣ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ማስታወሻዎች እና ያልተፈቀዱ ካልኩሌተሮች።
የመግቢያ መስፈርቶች
የ12ኛ ክፍል (ESSLCE)፦ ቢያንስ 300 (ወይም በየዓመቱ በትምህርት ሚኒስቴር የሚወጣው ማለፊያ ውጤት)።
የ UAT ማለፊያ ነጥብ፦
የመንግስት ስፖንሰርሺፕ እና ፕሬዚዳንሻል ስኮላርሺፕ፦ ቢያንስ 70%።
በራስ ወጪ (Self-Sponsorship)፦ ቢያንስ 60%።
ከፍተኛ ውድድር ያላቸው ዘርፎች፦ እንደ ህክምና እና ምህንድስና ያሉ ክፍሎች የበለጠ ከፍተኛ ውጤት ይፈልጋሉ።
የትምህርት እድል (Sponsorship) ዓይነቶች
የመንግስት ስፖንሰርሺፕ (ወጪ መጋራት)፦
ኢኮኖሚ አቅማቸው ደካማ ለሆኑ ተማሪዎች የተዘጋጀ።
ከወረዳ አስተዳደር የኢኮኖሚ አቅም ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ ያስፈልጋል።
ምደባው በአጠቃላይ የፍሬሽማን ዘርፍ (Natural ወይም Social Science) ላይ ይሆናል።
በራስ ወጪ መማር (Self-Sponsorship)፦
ከ2014 እስከ 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱና መክፈል የሚችሉ አመልካቾች።
ቀደም ሲል በሌላ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ (ከ2015-2017 ዓ.ም) ተመዝግበው የነበሩ የወጪ መጋራት እዳቸውን የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
እስከ 4 የሚደርሱ የትምህርት ዘርፎችን መምረጥ ይቻላል።
ፕሬዚዳንሻል ስኮላርሺፕ፦
ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የቀረበ።
በ12ኛ ክፍል 500 እና ከዚያ በላይ ያመጡ እና UAT ያለፉ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ በነጻ ይማራሉ።
ክፍያ እና ወጪዎች
የምዝገባና የፈተና ክፍያ፦ በአጠቃላይ 1,125 ብር የምዝገባ ክፍያ (ወይም 750 ብር የ UAT ፈተና ክፍያ በቴሌብር ይከፈላል)።
የራስ ወጪ ትምህርት ክፍያ፦ በ ECTS ክሬዲት ይሰላል (1,500 ብር በ 1 ECTS)። አንድ መደበኛ የ 35 ECTS ተርም 52,500 ብር ያስወጣል።
ካምፓሶች እና የትምህርት ዘርፎች
የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science)፦
4 ኪሎ፦ ኮምፒውተር ሳይንስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሒሳብ፣ ስታቲስቲክስ፣ ጂኦሎጂ።
5 ኪሎ (AAiT)፦ ምህንድስና (ሶፍትዌር፣ ሲቪል፣ ኤሌክትሪካል፣ ሜካኒካል፣ ኬሚካል)።
ጥቁር አንበሳ እና ጤና ሳይንስ፦ ህክምና፣ ፋርማሲ፣ ጤና መኮንን፣ የጥርስ ህክምና፣ ነርሲንግ።
ቢሾፍቱ፦ የእንስሳት ህክምና።
የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science)፦
6 ኪሎ (ዋናው ካምፓስ)፦ ህግ፣ ቋንቋዎች፣ ጋዜጠኝነት፣ ፖለቲካ ሳይንስ፣ ሶሺዮሎጂ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ስነ-ልቦና፣ ትምህርት።
FBE እና ኮሜርስ፦ አካውንቲንግ፣ ማኔጅመንት፣ ኢኮኖሚክስ፣ ፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን።
ስነ-ጥበብ (Alle School)፦ ስነ-ጥበብ፣ ቲያትር፣ ሙዚቃ፣ ዲዛይን።
የዶርምና የካፌ አገልግሎት
ከክልል የሚመጡ ተማሪዎች (መንግስት / ፕሬዚዳንሻል)፦ ነፃ የመኝታ እና የካፌ አገልግሎት ያገኛሉ።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፦ የዶርም እድላቸው ዝቅተኛ ነው (ተመላላሽ ይሆናሉ)።
በራስ ወጪ የሚማሩ ተማሪዎች፦ በወር 1,500 ብር ገደማ በመክፈል የዶርም አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
ምዝገባ
ምዝገባና ቲኬት፦ በ admission.aau.edu.et በመመዝገብ የ UAT ፈተና መግቢያ ቲኬት ማውረድ ይቻላል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ መረጃ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ምትፈልጉ በሙሉ ከኛ ጋር ጥናት ጀምሩ::
ለመመዝገብ: @AAUUATregisterbot
ለማንኛውም ጥያቄ 👇👇👇
@Uatadminbot
ለተያያዥ መረጃዎች Join us👇
@Uatprepare
@Uatprepare
1
1