🏆እንኳን ደስ አላችሁ🏆
🥇ተደገመ!!!🥇
እነሆ ሳምንትን ጠብቀዉ ሌሎቹ አብሪ ኮኮቦች ዛሬ ማን ከማን ያንሳል ብለዉ የዛሬ ሳምንት በስምንተኛ ክፍል ያየነዉን አስደማሚ ታሪክ መድገማቸዉ ብቻ ሳይሆን አሻሽለዉት ሌላ የደስታ ሳምንት ሰጡን።ለ6ተኛ መልቀቂያ ክልላዊ ፈተና የተቀመጡት ተማሪዋቻችን 100 % ወደ 7ተኛ ክፍል እጅግ በጣም ከፍተኛ በሆነ ዉጤት ተዘዋውረዋል። ይህ ዉጤት እንድመጣ የአንበሳዉን ድርሻ የተወጣችሁ መምህራን የፃፋችሁበት እጅ ወርቅ የቆማችሁበት እግር በረከትን ጉልበታችሁ ይባረክ።ለተማሪዎቹ የተለያየ ግብአትን በማቅረብና ስልጠናዎችን ከመስጠት እስከ መመረቅ ለነበራችሁ የአስተዳደር ሰራተኞችና መላዉ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ፈጣሪ የልፋታችሁን ዋጋ ይክፈላችሁ።በመጨረሻም አካዳሚያችንን አምናችሁ ዉድ ልጆቻችሁ ሰጥታችሁ በዛም በቂ ክትትል አድርጋችሁ የዛሬዋን ደስታ የተሰጣችሁ ወላጆች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን።😂😂😂❤️🙏❤️
🎓🎓የት/ቤቱ አስተዳደር🎓🎓

















