Emotion ማስተር ማድረግ በ ትሬዲንግ ዉስጥ ያለው ሚና ምንድነው? ሁላችንም በተለያየ ምክንያት ስሜታችንን… — TRADE INSIGHT AIRDROP — TG.ME

Emotion ማስተር ማድረግ በ ትሬዲንግ ዉስጥ ያለው ሚና ምንድነው? ሁላችንም በተለያየ ምክንያት ስሜታችንን Trigger ለሚያደርጉ ነገሮች ልንጋለጥ እንችላለን፤ ከነዛም ነገሮች በዋነኝነት በከባዱ ያገኘነውን ገንዘብ የምናጣ ከመሰለን በከፍተኛ ሁኔታ ስሜታዊ እንሆናለን። በተለምዶ Emotion ውስጥ ስንሆን Decision making/ውሳኔ የመወሰን አቅማችን ይዳከማል ልክ በጫካ ውስጥ ሊያጠቃን እንደተዘጋጀ አውሬ እራሳችንን ከሱ ለማትረፍ በእውር ድንብር ለማምለጥ እንደምንሞክረው ነገር ግ ን ትንሽ ቆም ብለን ከዛ ነገር survive ልናደርግበት የምንችልበትን መንገዶች ልናስብ አይቻለንም ምክኛቱም በዛ ሰአት የሚሰራው የአእምሮ ክፍላችን ስራው survive ስለማድረግ እንጂ ውሳኔ ንለመወሰን አይደለም። በትሬዲንግም ተመሳሳይ ነው ማርኬቱን እንደ አንድ በጫካ ዉስጥ እንዳለ አውሬ ቁጠሩት ገንዘባችሁን አንድ ትልቅ ማርኬት ሊያሳጣችሁ እንደሆነ ስታስገቡ ተረጋግቶ በማሰብ እና ሪስካችሁን ስለመቀነስ ሳይሆን በእውር ድንብር ገንዘባችሁን ለማዳን ትሯሯጣላቹ። ያው መጨረሻ ላይ ከናንተ አቅም በላይ በመሆኑ ገንዘባቹን ታጣላቹ። ለዛ ነው በ ዴሞ አንደኛ ሆናቹ በሪል አካውንት ሁሌ ተሸናፊ ምትሆኑት ችግሩ ከምታውቁት እውቀት ሳይሆን ከእናንተ ነው። በዚህም ምክንያት ነው ሁሌ እራሳቹ ላይ ስሩ የሚባለው። መልካም ቀን ተመኘውላችሁ። 🧑‍🎓 Mastering your Emotion Here:@Trade_Insight_Support

❤1👏1
August 9, 2025 155