Good Morning Ep 02 Crypto Currency ምንድነው? ክሪብቶ ካረንሲ ማለት "የምዕናብ ገንዘብ… — TRADE INSIGHT AIRDROP — TG.ME

Good Morning   Ep 02 Crypto Currency ምንድነው? ክሪብቶ ካረንሲ ማለት "የምዕናብ ገንዘብ ወይም የምዕናብ መገበያያ" ማለት ነው የምዕናብ ሲባል የማይጨበጥ የማይዳሰስና በኢንተርኔት ላይ የተቀመጠ ገንዘብ ሚለውን ለመግለፅ እንጅ እንደው ዝምብሎ የሕልምሀብት ማለት አይደለም ለምሳሌ የሞባይል ካርድ ገዝተን አየር ሰዓት ስንሞላ የሞላነው አየር ሰዓት ማይዳሰስ እና ማይጨበጥ ነው ነገር ግን ሲም ካርዳችን ላይ ሚቀመጥ ሀብታችን ነው አየርሰዓት ሲም ካርድ ላይ ሚቀመጥ ሀብታችን ሲሆን ክሪፕቶ ደግሞ ኢንተርኔት ላይ ሚቀመጥ ሀብታችን ማለት ነው። ይበልጥ እንዲቀለን ክሪብቶን በእንጀራ መስለን እንመልከተው ለምሳሌ ክሪፕቶ ማለት እንጀራ ነው ብላችሁ አስቡት ለምሳሌ ነው! ክሪፕቶ ከጀርባው እጅግ በረቀቁ ሚስጥራዊና ውስብስብ ኮዶች የተጠበቀ ነው እንጀራም እንጀራ ሆኖ ከመውጣቱ በፊት የተለያዩ የረቀቁ የመብላላት ሂደቶችን አልፎ ሚመጣ ሲሆን የእንጀራውን ጣዕም ሚጠብቁ እና ሚወስኑ የረቀቁ ኮዶች ብላችሁ ውሰዱት ክሪፕቶከረንሲ የባንክ ተቃራኒ ነው አንድ የበላይ ተቆጣጣሪ የለውም ሁሉም ነገር ሚመራው በተጠቃሚው ስምምነት ብቻ ነው በተመሣሣይ እንጀራም ተቆጣጣሪ የለውም አንዱን እንጀራ መርጦ ምርጥ ነው ብሎ ተፈላጊነቱ እንዲጨምር ሚያደርገውም ሆነ አልፈልገውም ብሎ ሚያራክሰው ተጠቃሚው ሕብረተሰብ ነው። 👇

👏4👍3
December 13, 2024 188