ቴንሃግ እና ሰራዊታቸው አሳዛኝ ታሪክ መጻፋቸውን ቀጥለዋል😞😔
❌ ማንቸስተር ዩናይትድ በኤፍ.ኤ ውድድር ከታችኛው እርከን በመጡ ክለቦች 2 እና ከ2 በላይ ግብ ሲቆጠርበት ከየካቲት 1996 በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። በ1996 ዩናይትድ ከሰንደርላንድ ጋር ካደረገው ግጥሚያ በኋላ እንደዚህ አይነት ውጤት አስመዝግቦ የማያውቅ ሲሆን፡ በትላንትናው የኒውፖርት ጨዋታ ይህን ታሪክ ማጻፍ ችሏል።
❌ በተጨማሪም ለመጀመርያ ጊዜ ከ4ኛ ዲቪዚዮን ቡድን ጋር ተጫውቶ 2 እና ከዝያ በላይ ግብ ሲያስተናግድ ከየካቲት 1970 ከኖርዝሃምፕተን ጋር ካደረገው ጨዋታ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ነው።
በእንግሊዝ የእግር ኳስ እርከን፡ ፕሪሚዬርሊግ፣ ቻምፒዮንሺፕ፣ ሊግ 1 እና ሊግ 2 ተብለው የሚከፋፈሉ ሲሆን፡ በትላንትናው ግጥሚያ ዩናይትድን ያስተናገደው ኒውፖርት ካውንቲ የ4ኛው እርከን (ሊግ2) ተሳታፊ ቡድን መሆኑ ይታወሳል።

7
3
1
1January 29, 2024 4.1K 1