በኬንያ የሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች ከድል በኋላ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ምስጋና አቀረቡ በኬንያ ርዕሰ መዲና… — Sport News/ስፖርት ዜና — TG.ME

በኬንያ የሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች ከድል በኋላ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ምስጋና አቀረቡ

በኬንያ ርዕሰ መዲና ናይሮቢ የሚገኙት የአርሰናል ደጋፊዎች ቅዳሜ እለት ባደረጉት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቡድናቸው ክሪስታል ፓላስን 5 ለ 0 በመርታቱ አድናቆትን ከማትረፍ ባለፈ በአንድ አጥቢያ ቤተክርስትያን በመሰባሰብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ደጋፊዎቹ የመድፈኞቹን ማሊያ ለብሰው በእሁድ ጠዋት አገልግሎት ላይ ቡድናቸው ላሳየው አስደናቂ ብቃት በደስታ ውዳሴ እና ምስጋና አቅርበዋል።በመጪው የውድድር ዘመን ለአርሰናል ቀጣይ ስኬት ተስፋ በማድረግ ጸሎት አቅርበዋል።

ከታዳሚዎቹ መካከል ጋዜጠኛ ኬኔዲ ሙሪቲ በፀሎት ስነ ስርዓቱ ላይ የተነሱትን ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያ ማጋራቱን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።የሰሜን ለንደኑ አርሰናል አንድ ጨዋታ ከሚቀረው ማንቸስተር ሲቲ እኩል እና ከሊቨርፑል በአምስት ነጥብ ዝቅ ብሎ ተቀምጧል።

ፎቶዎቹ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን የፈጠሩ ሲሆን አንዳንዶቹ በደጋፊዎች ላይ አፌዜዋለሁ፡፡

Via ዳጉ ጆርናል
🔥5❤4👍2👏2😍1
January 22, 2024 2.8K 1