Feven Gashaw: post #469 — TG.ME

እርግጥ ነው ዛሬ ዛሬ ከምንቀጥልበት የምንቆምበት ፣ከምንራመድበት የምንሸራተትበት ፣ከምንሮጥበት የምንደነቃቀፍበት ብዙ ምክንያት በህይወታችን ለመኖሩ እና ለመታየቱ ልባችን ምስክር ነው። ሆኖም ከምንቆምበትና ከምንወድቅበት ምክንያት ይልቅ የምንቀጥልበት ምክንያት ትልቅ ከሆነብን መቀጠል መታወቂያችን ይሆናል።ድሮም ኃይልን በሚሰጠን በእርሱ እንጂ ሀይልን በሰበሰብነው በእኛ ብቻ የሚሆን ነገር የለምና የተደገፍነውን እንመነው በእኛ ውስጥ ሆኖ ጀማሪውም ፈፃሚውም እርሱ ነው ።ከሚጥለን ይልቅ ብርቱ ፣ከሚያንሸራትተን ይልቅ ጠንካራ ፣የተስፋችን ሁሉ መደምደምያ፣ ቀና ብለን የምናየው የህልማችን እና የነገአችንን ባለቤትን ከያዝን ከሚጎትተን ሁሉ ጠንካራ፣ከሚከብደን ሁሉ ከባድ እንደሆንን የተገለጠ ነው። ክብደታችን የሚለካው ውስጣችን በተሸከምነው እንጂ ከውጭ በሚጎትተንም ሆነ በሚገፋን ነፋስ አይደለም! #ተስፋ #መቁረጥን #ተስፋ #የሚያስቆርጥ #ትውልድ ይታየኛል!!!!°°°°°°መልካም ሳምንት

August 4, 2025 1.8K 4