ጥበብ ከቁርኣን፡ የልጅ አስተዳደግ ጥበብ ከቁርኣን ልጆች ከአላህ የተሰጡን ውድ ስጦታና ታላቅ አደራ (አማና)… — AYA Media || አያ ሚዲያ — TG.ME

ጥበብ ከቁርኣን፡

የልጅ አስተዳደግ ጥበብ ከቁርኣን

ልጆች ከአላህ የተሰጡን ውድ ስጦታና ታላቅ አደራ (አማና) ናቸው። ይህን አደራ በአግባቡ መጠበቅና ለነገው ዓለም የሚጠቅም ሷሊሕ (ደጋግ) ትውልድን መፍጠር የእያንዳንዱ ሙስሊም ወላጅ ትልቁ ኃላፊነት ነው። ቁርኣን ይህንን ከባድ ኃላፊነት እንዴት መወጣት እንዳለብን የሚያመላክቱን በርካታ መመሪያዎችንና አስተማሪ ታሪኮችን ይዟል።

ከእነዚህም መካከል ጥቂቶቹን በማስተንተን ለልጆቻችን አስተዳደግ የሚረዱ ጠቃሚ ቁምነገሮችን ለማየት እንሞክራለን።

1. የእምነት መሰረት መጣል (ተውሒድ)


የልጅ አስተዳደግ ትልቁ ግብ ልጁን ከፈጣሪው ጋር ማስተዋወቅ ነው። ጥበበኛው ሉቅማን ለልጃቸው የመከሩት የመጀመሪያው ምክር ይህንኑ ያሳያል፦

"ሉቅማንም ለልጁ እርሱ እየገሰጸው «ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን) አታጋራ፡፡ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና»፡፡" (ሱረቱ ሉቅማን 31:13)

ከዚህ አንቀጽ የምንማረው፡-

ቅድሚያ ለተውሒድ፡

ለልጆቻችን ከምንም ነገር በፊት ማስተማር ያለብን የአላህን አንድነትና ብቸኛ ተመላኪነት፤ ከእርሱ ውጪ ማንም ሊመለክ እንደማይገባው ነው። ይህ የእምነታቸው መሰረትና የህይወታቸው መመሪያ ይሆናል።

በፍቅር የተሞላ ምክር፡

ሉቅማን ልጃቸውን "ልጄ ሆይ!" (ያ ቡነየ) በማለት በፍቅርና በእዝነት እንደመከሩ እናስተውላለን። ልጆችን ስናስተምር በጩኸትና በዛቻ ሳይሆን በፍቅርና በጥበብ መሆን ይኖርበታል።

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
Telegram
Hidaya Terbiya II ሂዳያ ተርቢያ
Hidaya Terbiya ሂዳያ ተርቢያ የመልካም ትውልድ ማፍርያ! @HidayaTerbiya
June 9, 2025 200 2
ጥበብ ከቁርኣን፡ የልጅ አስተዳደግ ጥበብ ከቁርኣን ልጆች ከአላህ የተሰጡን ውድ ስጦታና ታላቅ አደራ (አማና)… — AYA Media || አያ ሚዲያ — TG.ME