Sadat_Text_Posts: post #933 — TG.ME

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿وَاللَّهِ لَوْ تَعْلَمُونَ مَا أَعْلَمُ لَضَحِكْتُمْ قَلِيلًا وَلَبَكَيْتُمْ كَثِيرًا﴾
“ወላሂ! እኔ ማውቀውን ብታውቁ ኖሮ፣ ጥቂት ስቃችሁ ብዙ ባለቀሳችሁ ነበር።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 1044
*****

🚨በተለይ ሁለት ወቅቶችን ጠብቀህ ስገድ🚧

ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“ፀሀይ ከመውጣቷ እና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም።”
ማለትም፦ የፈጅርና የአስር ሶላቶች።

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 634
*****

የባሰ የከፋ ነው!

💎ብስራት የረሱልንصلى الله عليه وسلم) ሀዲስ ለሚያሰራጭ!

ረሱል (صلى الله عليه سلم) እንዲህ ብለዋል፦
﴿نضَّرَ اللهُ امرأً سمِعَ مَقالتي فبلَّغَها﴾
“አላህ ፊቱን ያብራለት ንግግሬን ሰምቶ ላደረሰው (ላስተላለፈው) ሰው።”
📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 189
*****

🤎 ልብህን ጠይቅ!

ከነውዋስ ኢብኑ ሰምዓን (رضي الله عنه) ተይዞ፡ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል፦
“በጎ ነገር ማለት መልካም ስነ-ምግባር ነው። ወንጀል ማለት በደረትህ ውስጥ የተመላለሰ እና ሰዎች በሱ ላይ ሆነህ ቢያዩህ የምትጠላው ነው።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2553
*****

⚠️⚠️ ከእሳት ውስጥ ነው…

ረሱል (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል፦
﴿ما كان أسفَلَ مِنَ الكَعبَيْنِ مِنَ الإزارِ؛ فهو في النّارِ﴾
“ልብሱን (ኢዛሩን) ከቁርጭምጭሚት በታች አውርዶ የለበሰ ከእሳት ውስጥ ነው።”
📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 5787
February 20, 2025 6.6K 18