የህፃናት ቆልማማ እግር (Clubfoot) 🦶
ምንድን ነው?
ቆልማማ እግር ምንድን ነው?
• ህጻናት ላይ በተፈጥሮ የሚከሰት፣ ሲወለዱ ጀምሮ የሚታይ የእግር መጣመም (መቆልመም) ነው።
• ከሚወለዱት 1,000 ህጻናት ውስጥ በ1 ወይም 2 ህጻናት ላይ ሊታይ ይችላል።
• በወንዶች ህጻናት ላይ ከሴቶች በበለጠ ይከሰታል።
• በግማሽ የሚሆኑት ህጻናት ላይ በሁለቱም እግሮች ላይ ሊገኝ ይችላል።
➪ ምልክቶች
🔹 የእግር ወደ ውስጥ መዞር
🔹 የባት እና የእግር መጠን መቀነስ
🔹 ያልተለመደ የቆዳ እጥፋት መኖር
🔹 ተገቢ የሃኪም ምርመራ ማድረግ ችግሩ መኖሩን ለማወቅ ያስችላል።
➪ አይነቶች
1. ምክንያቱ የማይታወቅ (Idiopathic)፣ በአብዛኛው የሚከሰተው አይነት ነው።
2. ከነርቭ ጉዳት ጋር ተያይዞ የሚመጣ (Neurogenic)
3. ከሌሎች አካላዊ ችግሮች ጋር የሚያያዝ (Syndromic)
➪ ህክምና አለው?
ህክምናው ህጻኑ ከተወለደ በኋላ ከ1 እስከ 2 ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲጀመር ይመከራል። ህክምናው ሶስት ክፍሎች አሉት።
1. በየሳምንቱ የሚቀየር ጀሶ
ሃኪሙ በየሳምንቱ በጥንቃቄ የዞረውን እግር ቀስ በቀስ በማዞር እና በጀሶ ወደ ትክክለኛ ቦታው ይመልሰዋል። ይህም በትንሹ ከ5 እስከ 6 ሳምንት ሊወስድ ይችላል።
2. ቀላል የጅማት ቀዶ ህክምና
ከ80 እስከ 90 በመቶ የሚሆኑት ልጆች ሊያስፈልጋቸው ይችላል።
3. የእግር ጫማ ድጋፍ
የጀሶ ህክምናው ካለቀ በኋላ ህፃናት ጫማውን በመጀመሪያዎቹ 3 ወራት ለ24 ሰዓት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ከዚያ በኋላ አራት ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ ማታ ማታ ማድረግ አለባቸው።
❗ ጫማውን ሃኪም በሚያዘው መሰረት አለማድረግ የቆልማማ እግር መልሶ መከሰት ሊያመጣ ይችላል።
🚫 ቆልማማ እግር ፀሐይ በማሞቅ፣ በማሳሸት ወይም በራሱ ሊስተካከል አይችልም።
🤱 እናቶች ጨቅላ ህጻናት ሲወለዱ የተጣመመ (የተቆለመመ) እግር ካስተዋሉ ለህክምና ባለሙያ ያሳዩ።
ለሁሉም ወላጆች 👨👩👧👦 ይህ 👁️🗨️ መረጃ ይደርስ ዘንድ Share ያድርጉት።
በዶ/ር ዳዊት አለማየሁ
በቅዱሰ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
የህጻናት አጥንት ቀዶ ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት
#clubfootawareness #AaBET #SPHMMC #MOH #Orthopedics #pediatricsorthopedics
September 2, 2026 1.2K 5