ትዝብት የሚያጠቃኝ አይነት ሰው ነኝ.... በሄድኩበት ሁሉ የምታዘብ...
የተቀመጠውን በሀሳብ ጭልጥ ያለውን
የቆመውን የሚሄደውን ሁሉንም የሰው ፍጥረት እታዘባለሁ.....
እንዴት ታዘብኩ አላቅም... በዛው ቅፅበት ካልሆነ ቆይቶ ትዝ አይለኝም
ምታዘበው የሰው ፍጥረት ባጣ ስለትንፋሼ አስባለሁ እሱንም እገመግማለሁ አለፍ ሲል ሰው ትከሻ ጀርባ አልያ ጭንቅላት ላይ ስላረፈች ዝንብ እታዘባለሁ........
እንዴት ፈጠራት ለምን ቆሻሻ ወደደች እኛው ገፋፍተናት ወይ አፈጣጠሯ......
ብዙ ብዙ ገምታለሁ መጨረሻው ዞሮ ላይገባኝ ስለሁላችን ፍጥረታት ለማወቅ እታገላለሁ.....
ለለምን መልስ ለማግኘት.....
አንዷ ለምን ስለዘራቻቸው ብዙ ሺህ የለምን ክምር መልስ ለማበጀት ከማልቀድመው አምላክ ጋ እሮጣለሁ..