አንድ ሰውን በደንብ ታውቃለህ ብዙ ጊዜ አብራችሁ አሳልፋችኋል ብዙ ትዝታዎች አሏችሁ ግን ከዚያ ተለያያችሁ።
ከወራት በኋላ እሱን ስታስብ፣ አእምሮህ የሚያመጣው ብዙ ጊዜ የመጨረሻውን ጊዜ ነው ለምን ይመስልሀል?
Recency Effect
በሳይኮሎጂ Recency Effect የሚባል ክስተት አለ።
ይህም ከቅርብ ጊዜ የተከሰቱ ነገሮችን ከቆዩ ነገሮች ይልቅ በቀላሉ የማስታወስ አዝማሚያ ነው።
ለምሳሌ፣ አንድ ሰው 10 ነገሮችን ቢነግርህ፣ የመጨረሻዎቹን ጥቂት ነገሮች ማስታወስህ ከመጀመሪያዎቹ ይልቅ ቀላል ሊሆን ይችላል።
ግን ይህ በትዝታ ብቻ አይቆምም።
የምንሰጠውን ውሳኔ፣ ሰዎችን የምንገመግምበትን መንገድ እና አንድን ክስተት የምናስታውስበትን መንገድም ሊነካ ይችላል።
ስለ ግንኙነትስ?
አንድ ሰው ለዓመታት ጥሩ ሰው ሆኖ ኖረህ። ነገር ግን በመጨረሻ ከአንተ ጋር አንድ መጥፎ ነገር አደረገ።
ከዚያ በኋላ ስለእሱ ስታስብ፣ ያ የመጨረሻው ክስተት ላይ ጥገኛ ትሆናለህ ። “እሱ ሁልጊዜ እንደዚህ ነበር” ብለህ ልታስብም ትችላለህ።
ነገር ግን የሰውዬው ሙሉ ታሪክ ከዚያ የመጨረሻ ክስተት የበለጠ ሰፊ ነው።
@PsychologyCentral