በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የዝናብ ሁኔታ ተከትሎ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄዎችን አድርጉ ሲል የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ፡፡
ኮሚሽኑ የጥንቃቄ መልእክቱን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያጋራ ሲሆን ህብረተሰቡ በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የዝናብ ሁኔታ ተከትሎ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄ ያድርግ ሲል አሳስቧል፡፡በዚህም በወንዝ ዳርቻና ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች የውኃው መጠን ከመጨመሩ በፊት ጥንቃቄ ያድርጉ ብሏል።
በሉላ በኩልም የውኃ መውረጃዎችን መፈተሸ፣ በቤት ዙሪያ ያሉ ቦዮች በቆሻሻ አለመደፈናቸውን ማረጋገጥ እና የልጆችን ውሎ መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል።
ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ልጆች ከቤት እንዳይወጡና ወደ ዋና ዋና የጎርፍ መውረጃዎች እንዳይጠጉ መቆጣጠር ይገባል ተብሏል፡፡
አደገኛ የጎርፍ ምልክት በሚታይበት ወቅት በአደጋ ጊዜ ስልክ 939 ላይ በመደወል ያሳውቁ ሲል ኮሚሽኑ አሳስባል።
1August 18, 2026 68